1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢንጅነር ስመኘው ሞት ሃዘንና ቁጣዉ እንደቀጠለ ነዉ

ዓርብ፣ ሐምሌ 20 2010

አዲስ አበባ የሚገኙ የኢንጅነር ስመኘው በቀለ ቤተሰቦች በኢንጂኔሩ አሟሟት በከባድ ሐዘን ላይ መሆናቸዉ ተሰማ። በተለያዩ የኢትዮጵያዉያ ክፍሎች በተለይም በኢንጅነር ስመኘው በቀለ የትዉልድ ቦታ በጎንደር ኢትዮጵያዉያን ሃዘናቸዉን እና ቁጣቸዉን መግለፃቸዉን እንደቀጠሉ ነዉ ።

https://p.dw.com/p/32DER
Äthiopien, Simegnew Bekele, Projektleiter des Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD)
ምስል DW/T.Waldyes

ፖሊስ በጥይት ተመተው መሞታቸውን አረጋግጦአል።

ፖሊስ ሃሙስ ሐምሌ 19 ፤ 2010 ዓ,ም በሰጠው መግለጫ በጥይት ተመተው መሞታቸውን አረጋግጦአል። ኢንጅነር ስመኘው ከጠዋቱ 2 ሰዓት ከ20 አካባቢ መስቀል አደባባይ ከዋናው መንገድ ገባ ብሎ በሚገኘው ቦታ ይዘውት በነበረው ቪ 8 መኪና ውስጥ በመሪው መቀመጫ ሞተው መገኘታቸውን ነዉ የገለፀዉ። በኢንጅነር ስመኘው ሞት የኢትዮዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር፤ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት፤  የኢህአዴግ ምክር ቤት የክልል መንግሥታት እና ሌሎችም ተቋማት የሀዘን መግለጫዎችን አውጥተዋል። ዛሬም የኢንጂኔሩ ሞት ከፍተኛ መነጋገርያ ሆኖ ነዉ የዋለዉ፤ የፊታችን እሁድ ሐምሌ 22 የቀብር ስነስርዓታቸዉ እንደሚፈፀም ተመልክቶአል። በኢንጂኔሩ ሞት ያለዉን ሁኔታ የአዲስ አበባዉን ወኪላችንን በስልክ ጠይቀነዉ ነበር። 

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ 

ነጋሽ መሐመድ