1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፍርንክፈርቱ ዐውደ ጥናት

ዓርብ፣ ጥር 15 2012

በኢትዮጵያ በርካታ የጀርመን የጨርቃጨርቅ አልባሳትና የቆዳ ውጤቶች አምራቾች መሰማራታቸው በዐውደ ጥናቱ ተገልጿል። አልፎ አልፎ በአገሪቱ የሚታየው የሕዝቦች መፈናቀል፣ የሰላም እጦት እና አለመረጋጋትና ሌሎችም  ችግሮች በኢንዱስትሪው ዕድገት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ በማሳደሩ መንግሥት ለችግሮቹ ትኩረት እንዲሰጥ ተጠይቋል።

https://p.dw.com/p/3Wmef
Deutschland Business Workshop African Association of German in Frankfurt
ምስል DW/Endalkachew Fekade

በኢትዮጵያ የጨርቃጨርቅ አልባሳትና የቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪ

የኢትዮጵያው ለውጥ የጨርቃጨርቅ አልባሳትና የቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ለማሳደግ የሚያበረታታና ዓለም አቀፍ ባለወረቶችንም ለኢንቨስትመንት የሚጋብዝ መሆኑ ተገለፀ ።ይህ የተገለጸው የጀርመን የኢኮኖሚ ጉዳዮችና የኢነርጂ ሚኒስቴር ከአፍሪቃውያን የጀርመን ንግድ ማህበር ጋር በመተባበር በኢንዱስትሪው ክፍለ ኢኮኖሚ ለተሰማሩ የጀርመን ባለሀብቶች ለንግድ ጥናት ምርምርና አማካሪ ድርጅቶች ለኢትዮጵያውያን እና በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሙያዎች በፍራንክፈርት ከተማ ባዘጋጁት የ 2020 ዓ.ም የኢትዮጵያ የፓይለት ፕሮጀክት ዐውደ ጥናት ላይ ነው ።በኢትዮጵያ በርካታ የጀርመን የጨርቃጨርቅ አልባሳትና የቆዳ ውጤቶች አምራቾች መሰማራታቸው በዐውደ ጥናቱ ተገልጿል። አልፎ አልፎ በአገሪቱ የሚታየው የሕዝቦች መፈናቀል፣ የሰላም እጦት እና አለመረጋጋትና ሌሎችም  ችግሮች በኢንዱስትሪው ዕድገት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ በማሳደሩ መንግሥት ለችግሮቹ ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል:: ዝርዝሩን እንዳልካቸው ፈቃደ አጠናቅሮታል::
እንዳልካቸው ፈቃደ 
 ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ