1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ የሰላም ግንባታ የሴቶችን ሚና እንዴት ማሳደግ ይቻላል?

ሐሙስ፣ ሰኔ 23 2014

የብሪታኒያው ቻታም ሐውስ በትላንትናው ዕለት በኢትዮጵያ የሰላም ግንባታ የሴቶችን ሚና እንዴት ማሳደግ ይቻላል በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ በኢንተርኔት አማካኝነት የተካሔደ ውይይት አዘጋጅቶ ነበር። የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እና በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች የሚቀሰቀሱ ግጭቶች በተለይ በሴቶች ላይ ብርቱ ተጽዕኖ ማሳደራቸውን ቻታም ሐውስ ገልጿል።

https://p.dw.com/p/4DU2Y
Äthiopien | Amhara Region in Artuma
ምስል Eric Lafforgue/imago images

በኢትዮጵያ የሰላም ግንባታ የሴቶችን ሚና እንዴት ማሳደግ ይቻላል?

የብሪታኒያው ቻታም ሐውስ ወይም የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ሮያል ኢንስቲትዩት በትላንትናው ዕለት በኢትዮጵያ የሰላም ግንባታ የሴቶችን ሚና እንዴት ማሳደግ ይቻላል በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ በኢንተርኔት አማካኝነት የተካሔደ ውይይት አዘጋጅቶ ነበር። 

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እና በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች የሚቀሰቀሱ ግጭቶች በተተለይ በሴቶች ላይ ብርቱ ተጽዕኖ ማሳደራቸውን ቻታም ሐውስ ገልጿል። ተቋሙ እንደሚለው አካላዊ እና ወሲባዊ ጥቃት፣ መፈናቀል፣ የትምህርት መቋረጥ በሴቶች ላይ ከበረቱ ዳፋዎች መካከል ናቸው። 

በውይይቱ ተመራማሪ እና የጾታ ፖሊሲ ባለሙያ የሆኑት ሕሊና ብርሐኑ፣ ኢስት አፍሪካን ኢንሺየቲቭ ፎር ቼንጅ የተባለው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ዳይሬክተር ለሚ ስሜ፣ ጀርመናዊቷ የፖሊሲ አማካሪ እና ኢንክሉሲቭ ፒስ የተባለው በሰላም ላይ የሚሰራ ተቋም ዳይሬክተር ታንያ ፋንሆልዝ እንዲሁም የሥርዓተ ጾታ ባለሙያው ንጉሴ ምኅረቱ ተሳትፈዋል። ውይይቱን የመሩት በቻታም ሐውስ የአፍሪካ ፕሮግራም ምክትል ዳይሬክተር ትግስቲ አማረ ናቸው ድልነሳው ጌታነህ ውይይቱን ተከታትሎት ነበር። 

ድልነሳው ጌታነህ
እሸቴ በቀለ
አዜብ ታደሰ