1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እገዳና መዘዙ

ሐሙስ፣ መጋቢት 7 2015

«እገዳውን አልፈው መግባት በሚያስችሉ ሶፍትዊሮች ምክንያት ኮምፒውተራችን በቫይረስ ከመጠቃቱ ባሻገር በግለሰብም ሆነ በመንግስት ደረጃ በቀላሉ የመረጃ ምንተፋ ሊደርስ ይችላል » «ቴሌ ለትርፍ የተቋቋመ ድርጀት እስከሆነ ድረስ አቀርበዋለሁ ሲል ውል ለገባለት አገልግሎት ተጠያቂ ነው ''

https://p.dw.com/p/4OmKe
Symbolbild Soziale Netze
ምስል Axel Heimken/dpa/picture alliance

በኢትዮጵያ በርካታ ተጠቃሚ ያለቸው ቴሌግራም ፣ ፌስቡክ ፣ ዩትዩብ  ቲክቶክ እና መሰል የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እስካሁን በይፋ ባልተነገረ ምክንያት ገደብ ተደርጎባቸው አገልግሎት ካቆሙ ከአንድ ወር በላይ ሆኗል።በእነዚህ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ለምን ገደብ እንደተጣለ ሀላፊነቱን ወስዶ የተናገረ የመንግስት አካል አለመኖሩ ብቻ ሳይሆን  ገደቡ መቼ እንደሚነሳ  የሚታወቅ ነገር የለም። በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎቹ ላይ የተጣለው እገዳ መዘዝ በቀላሉ የሚታይ እንዳልሆነ ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የሕግ ባለሞያ አስረድተዋል።

ቲክቶክ ቴሌግራም ፣ ፌስቡክ ዩትዩብ እና ሌሎችም የማህበራዊ መገናኛዎች  በ ኢትዮ ቴሌኮም  ሆነ በቅርቡ በኢትዮጵያ የቲሌኮም አገልግሎት ሊሰጥ በገባው  በሳፋሪ ኮም በኩል ከአገልግሎት ከመስጠት ተገድበዋል። በዚህም ምክንያት በተላያየ የቲክኖሎጂ ትስስር ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ' በስራቸው ላይ እንቅፋት ከማጋጠሙም ባሻገር የከፈልንበትን አገልግሎት ማግኘት አልቻልንም' ይላሉ። በኮምፒውተር ስራ ላይ የተሰማራው ወጣት ባለሙያ እስካሁን በይፋ ባልተነገረ ምክንያት ለረጅም የቆየው እገዳ  ስራቸውን አስቸጋሪ እንዳደረገው ለ DW እንዲህ ሲል ይናገራል

እገዳውን አልፈው መግባት የሚያስችሉ ቲክኖሎጂዎች ሶፍትዊሮች በአብዛኛው ነፃ ስለሆኑ ኮምፒውተራችን  በቫይረስ ከመጠቃቱ ባሻገር  በቀላሉ የመረጃ ምንተፋ በግለሰብም ሆነ በመንግስት ደረጃ ሊከሰት ይችላል ሲል ጉዳቱን ገልጿል ።

''ያለበቂ ምክንያት በአንድ ሀገር ዲሞክራሲን ለመገንባት እሰራለሁ ከሚል መንግስት ተጨባጭ መረጃ እና ማስረጃ በሌለበት የተጣለው መረጃን መገደብ ወይም መከልከል የኢትዮጵያ ህገመንግስት ላይ የሰፈረውን  የህብረተሰቡን መብት መጣስ ነው'' ሲሉ ለ DW የተናገሩት አቶ ደበበ ኃ ∕ ገብርኤል የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ'' ቴሌ ለትርፍ የተቋቋመ ድርጀት እስከሆነ ድረስ አቀርበዋለሁ ሲል ውል ለገባለት አገልግሎት ተጠያቂ ነው ''ሲሉ ይናገራሉ

እንዲህ አይነቱ ገደብ እና ክልከለ  አሁን በሀገር ውስጥ አገልግሎቱን በመስጠት ላይ ያሉት ድርጅቶችን ኢትዮ ቴሌኮምን ብቻ ሳይሆን ወደፊት ወደሀገር ውስጥ ለ ስራ ሊገቡ ያሰቡ ድርጅቶችንም ፍላጎት ይቀንሳል የሀገርንም ገጽታ ያበላሻል ሲሉ የተናገሩት የህግ ባለሙያ ምናልባት ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪኮም  በዚህ ክልከላ ለደረሰባቸው ኪሳራ መንግስትን ሊጠይቁ ይችላሉ ሲሉ ገልፅዋል። የቴሌኮም አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች የቀን ፣የሳምንት፣ የወር እና የዓመት የሚሉ የተለያየ የአገልግሎት ኮንትራት ለደንበኞቻቸው ያቀርባሉ ላለፉት 4 ሳምንታት አንድ ወር ወይም 30 ቀናት  የአገልግሎት ውል ገብተው ቅድመ ክፍያ የፈጸሙ ደንበኞች ያገኙት  ውስን እና የተቆራረጠ አገልግሎት ነው። ያነጋገርኳችው ደንበኞች ተስፋ የሚያደርጉት ያልተጠቀሙበት አገልግሎት ማስተካከያ ይደረግበታል የሚል ነው

ቲክቶክ፣ ቴሌግራም ፣ ፌስቡክ ፣ዩትዩብ እና ሌሎችም የማህበራዊ መገናኛዎች በኢትዮ ቴሌኮም  ሆነ በቅርቡ በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ሊሰጥ በገባው  በሳፋሪ ኮም በኩል ከአገልግሎት ከመስጠት ተገድበዋል ያም ሆኖ የተለያዩ የመንግስትም ድርጅቶች ሆነ ግለሰቦች በVPN በተሰኘ ሲስተም  በማለፍ አገልግሎት እየተጠቀሙ ይገኛሉ ። ትዊተር ኢንስታግራም እና ሊንክንደን  የተሰኙት የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በኢትዮጵያ ከተጣለው ገደብ ያመለጡ  የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች መካከል ናቸው ።

ሀና ደምሴ

ኂሩት መለሰ 

አዜብ ታደሰ