1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ኮንፈረን በመቐለ

ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 6 2011

በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሚመክር ኮንፈረን በመቐለ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በመካሄድ ላይ ነው፡፡ በካንፈረንሱ 15 ተቃዋሚ የፖለቲካ ፖርቲዎች፣ ምሁራን፣ ታዋቂ ግለሰቦችና የተለያዩ የማሕበረሰብ ክፍል ተወካዮች ተገኝተውበታል፡፡

https://p.dw.com/p/3ACH0
Äthiopien Konferenz in Mekelle
ምስል DW/M. Haileselassie

ኮንፈረንሱ ነገም ይቀጥላል

በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሚመክር ኮንፈረን በመቐለ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በመካሄድ ላይ ነው፡፡ በኮንፈረንሱ 15 ተቃዋሚ የፖለቲካ ፖርቲዎች፣ ምሁራን፣ ታዋቂ ግለሰቦችና የተለያዩ የማሕበረሰብ ክፍል ተወካዮች ተገኝተውበታል።ኮንፈረንሱ በዛሬው ውሎው የቀድሞ ብአዴን ታጋይና የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን አቶ በረከት ስምኦን ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ መነሻነት ተወያይቷል፡፡ አቶ በረከት ስምኦን ኢትዮጵያ በከባድ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ችግር እንዳለች በጽሑፋቸው ጠቁመዋል። የሕግ የበላይነት ማረጋገጥ፣ ፅንፈኛ ብሄርተኝነት መግራት፣ የወጣቶች ጥያቄ መመለስ፣ የውጭ ጣልቃ ገብነት ማስወገድ፣ ጠንካራና ዴሞክራስያዊ መንግስት መፍጠር በዋነኝነት ሀገሪቱ የምትሻቸው አንገብጋቢ ጥያቄዎች መሆናቸው አቶ በረከት ስምኦን ገልፀዋል፡፡በቀረበው ፅሁፍ ተሳታፊዎች ሀሳብና ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ኮንፈረንሱ ነገም የሚቀጥል ሲሆን፤ ሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች ይነሱበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ