1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩናይትድ ስቴትስ አዲስ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት

እሑድ፣ ግንቦት 8 2013

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልታማን ካለፈው ሳምንት አጋማሽ አንስቶ እስከዚህ ሳምንት መጀመሪያ ድረስ ከግብጽ ሱዳን ኤርትራና ኢትዮጵያ መሪዎችና ዲፕሎማቶች ጋር ውይይት አካሂደዋል።የአዲሱ የአሜሪካን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ምንነት፣ ፋይዳው እድሎችና ተግዳሮቶቹ የዛሬው እንወያይ ትኩረት ነው።

https://p.dw.com/p/3tRnj
Jeffrey Feltman UN-Untergeneralsekretär
ምስል Getty Images/AFP/R. Arboleda

እንወያይ፦ በአፍሪቃ ቀንድ የዩናይትድ ስቴትስ አዲስ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት

ዩናይትድ ስቴትስ «በታላቁ ህዳሴ ግድብ ምክንያት የተፈጠረውን ውዝግብ ለመፍታት ያለመ» ያለችውን አዲስ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በአፍሪቃ ቀንድ ጀምራለች።የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልታማን ካለፈው ሳምንት አጋማሽ አንስቶ እስከዚህ ሳምንት መጀመሪያ ድረስ ከግብጽ ሱዳን ኤርትራና ኢትዮጵያ መሪዎችና ዲፕሎማቶች ጋር ውይይት አካሂደዋል።በኢትዮጵያ ጉብኝታቸውም ከኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር በታላቁ ህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር፣በኢትዮ ሱዳን ድንበር ጉዳይ እንዲሁም በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ላይ እንዲሁም ስለ ስድሰተኛው ብሔራዊ ምርጫ መነጋገራቸው ተዘግቧል። የአዲሱ የአሜሪካን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ምንነት፣ ፋይዳው እድሎችና ተግዳሮቶቹ የዛሬው እንወያይ ትኩረት ነው።

በዚህ ርዕስ ላይ የሚወያዩ አራት እንግዶችን ጋብዘናል እነርሱም ክቡር አምባሳደር ፍጹም አረጋ በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር፣ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ የቀድሞ የኢትዮጵያ ዲፕሎማትና በአሁኑ ጊዜ በኖርዝ ካሮላይና ስቴት ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር፣ፕሮፌሰር ካሳሁን ብርሃኑ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ እንዲሁም የፖለቲካ ተንታኝና ጋዜጠኛ ቻላቸው ታደሰ ናቸው።

ሙሉውን ውይይት የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ማድመጥ ይቻላል።

ኂሩት መለሰ