1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአፋር ክልል ግጭት 10 ሰዎች ተገደሉ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 17 2011

በአፋር ክልል ውስጥ በተከሰተ ግጭት የሰዎች ሕይወት ጠፋ። በክልሉ ዞን አራት ገዋኔ ወረዳ በሚገኙ የተለያዩ ቦታዎች ትናንት በተቀሰቀሰው ግጭት 10 ሰዎች በመኪና ሲጓዙ በላውንቸር ተመትተው መሞታቸውን የዓይን እማኞች ከአካባቢው ለDW ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/3AejT
Afar-Region in Äthiopien
ምስል picture-alliance / africamediaonline

ግጭቱ ላለፉት ሦስት ቀናት ዘልቋል

ላለፉት ሦስት ቀናት በዘለቀው ግጭት የሟቾች ቁጥር ከ20 በላይ እንደሚዘልል፤ ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው ወገኖች ደግሞ ቆስለው ህክምና ላይ መሆናቸውም ተነግሯል። የክልሉ ነዋሪዎች በአካባቢው ተደጋጋሚ ጥቃት ቢደርስም የመከላከያ ሠራዊት ተገቢ ያሉትን ጥበቃ አላደረገልንም ሲሉም አመልክተዋል። የሀገር የመከላከያ ሚኒስቴር የሚዲያዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በበኩሉ ስለጉዳዩ መረጃ የለኝም ብሏል። ከአዲስ አበባ ዮሐንስ ገብረ እግዚአባሔር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአባሔር

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋኅ መሐመድ