በአገራዊ ጉዳዮች ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት
ሐሙስ፣ ጥቅምት 5 2013ማስታወቂያ
በፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የታቀፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሕገ መንግሥት እና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት፣ በፓርቲዎች አደረጃጀትና ችግሮቻቸው፣ ኢትዮጵያ ውጥ በሚስተዋሉ የፖለቲካ ቅራኔዎች እንዲሁም ነፃ እና ትክክለኛ ምርጫ እንዴት ማካሔድ ይቻላል በሚሉ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ውይይት አድርገዋል። በውይይቱ አገራዊ መግባባት መፍጠርና አገርን እየጎተተ ያለን ሽኩቻን በማስወገድ ሕዝብ ሊጠቀም በሚችልባቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ እንዲደረስ ተጠይቋል። በውይይቱ መክፈቻ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተገኝተዋል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ