1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርትአፍሪቃ

በአዲስ አበባ የት/ቤቶች ክፍያ ጭማሪ ሮሮ

ሐሙስ፣ ግንቦት 3 2015

በአዲስ አበባ የሚገኙ የትምህርት ተቋዋማት ለመጭው ዓመት ትምህርት የተማሪዎች ክፍያ እስከ 100% የሚደርስ ጭማሪ ማድረጋቸው በርካታ ወላጆችን አእስቆጥቷል ። የትምህርት እና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን የ2016 ዓ.ም የትምህር ቤት ክፍያ ጭማሪ ከወላጆች ጋር በቂ መግባባት ላይ ሳይደርስ ወደ ተግባር መግባት እንደማይቻል ዐሳውቋል ።

https://p.dw.com/p/4REAz
Äthiopien Addis Abeba Stadtansicht
ምስል Solomon Muchie/DW

ከፍተኛው ጭማሪ በርካታ ወላጆችን አእስቆጥቷል

በአዲስ አእበባ የሚገኙ የግል እና የመንግስት ያልሆኑ የትምህርት ተቋዋማት ለመጭው ዓመት ትምህርት የተማሪዎች ክፍያ እስከ 100% የሚደርስ ጭማሪ ማድረጋቸው በርካታ ወላጆችን አእስቆጥቷል ።  የትምህርት እና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን የ2016 ዓ.ም የትምህር ቤት ክፍያ ጭማሪ ከወላጆች ጋር በቂ መግባባት ላይ ሳይደርስ ወደ ተግባር መግባት እንደማይቻል ዐሳውቋል ።

ሰሞኑን በርካታ የግል እና መንግስታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት ለመጭው ዓመት የትምህርት ዘመን ክፍያ ጭማሪ ማድረጋቸው ወላጆችን አስቆጥቷል ። በሁሉም አቅጣጫ የኑሮ ውድነት በየግዜው ማሻቀብ መተንፈሻ ያሳጣው ወላጅ ትምህርት ቤቶች ባደረጉት ጭማሪ አቤት የምንልበት   ቸግሮናል ይላሉ ።
 
ለ2016 የትምህርት ዘመን የክፍያ ጭማሪ ያደረጉት የግል እና መንግስታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት    እስከ 100% እንደሆነ ወላጆች ይናገራሉ ። ትናንት የትምህርት እና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን በአዲስ አበባ ለሚገኙ የግል እና የመንግስት ላልሆኑ ትምህርትቤቶች በፃፈው ደብዳቤ የ2016 የትምህር ቤት ክፍያ ጭማሪ ከወላጆች ጋር በቂ መግባባት ላይ ሳይደርስ ወደ ተግባር መግባት እንደማይቻል ዐሳውቋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ ከፊል ገጽታ
የአዲስ አበባ ከተማ ከፊል ገጽታምስል Seyoum Getu/DW

ባለስልጣኑ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር ለሚገኙ የግል እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ትምህርት ቤቶች በጻፈው ደብዳቤ፤ የ2016 የክፍያ ጭማሪ በተመለከተ ከሁሉም ት/ቤት ባለቤቶች ጋር ባደረግነው ውይይት መሠረት፤ የክፍያ ጭማሪው በት/ቤቱ እና በወላጆች ውይይት እና መግባባት ላይ መሠረት ያደረገ እንዲሆን በጋራ መሥማማት ላይ ተደርሶ የነበር ቢሆንም በመዲናይቱ ያሉ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር በቂ ስምምነት ላይ ሳይደርሱ የክፍያ ጭማሪ ማድረጋቸውን ባለስልጣኑ አረጋግጫለሁ ብሎዋል ፣ ይህንንም ተከትሎ በመጭው አመት የሚጀመረውን የትምህርት ዘመን ክፍያ ጭማሪን በተመለከተ ከወላጆች ጋር   መግባባት ላይ ሳይደርስ ወደ ተግባር መግባት እንደማይቻል አሳስቦዋል ።

የትምህርት እና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን ይህንን ይበል እንጂ በከተማዋ ያሉ የተለያዩ የግል እና መንግስታዊ ያልሆኑ ትምህርት ቤቶች የመጪውን የትምህርት ዘመን ክፍያ ጭማሪ አውጥተው ለተማሪዎቻቸው ወላጆች ያሳወቁ ተቋማት ቁጥር ብዙ ነው ይህ ብቻ ሳይሆን ትምህርት ቤቶች ወላጆችን ጠርተው ጭማሪውን ባሳወቁበት ስብሰባ ላይም የትምህርት ሚንስትር ተወካዮች በቦታው ተገኝተው ነበር ፣ ይላሉ DW ያናገራቸው ወላጆች ጭማሪው የህዝቡን ኑሮ ያላገናዘበ ነዋሪውን ወደ ማያልቅ ችግር እና ፈተና ውስጥ የከትት ነው ይላሉ ፣ 

የዋጋ ጭማሪውን ለማድረግ የተገደዱበትን ምክንያት እንዲነግሩኝ የጠየኳቸው 3 ትምህርትቤቶች ሁሉም በተመሳሳይ ለግዜው ምንም አስተያዬት ለሚዲያ መስጠት አንፈልግም ብለዋል ነገር ግን መጨመር ያስፈለገበትን ምክንያት በላኩልኝ መረጃ መሰረት በኮቪድ 19 ወረርሺኝ ምክንያት ባለፉት 2 አመታት ምንም አይነት ክፍያ ያልጨመርን በመሆናችን እና በሀገሪቱ ላይ ያለው የዋጋ ንረት እንደዚሁም የብር የመግዛት አቅም  ማሽቆልቆል  የምንዛሬ እጥረት  እና ተያያዥ ምክንያቶች የትምህርት ተቋማቱ የ ክፍያ ጭማሪ ለማድረግ መገደዳቸውን ይናገራሉ ።

ሐና ደምሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሰ