1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአዲስ አበባ ሳይለሙ ቆዩ የተባሉ ቦታዎች አጥር መፍረስ

ረቡዕ፣ ኅዳር 12 2011

የአዲስ አበባ ከንቲባ የፕሬስ ሴክረታርያት ወ/ት ፌቨን ተሾመ ለDW እንዳስረዱት እርምጃው የተወሰደው የአዲስ አበባ ካቢኔ መስከረም 12፣2011 ዓም 154 ቦታዎች ውላቸው ተቋርጦ ለከተማ አስተዳደሩ እንዲመለሱ በወሰነው መሠረት ነው።

https://p.dw.com/p/38gam
Äthiopien - Addis Abeba - City Churchill Road
ምስል DW/Y. Geberegziabehr

ቃለ ምልልስ ከወ/ት ፌቬን ተሾመ ጋር

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ለዓመታት ሳይለሙ ተይዘው የቆዩ የተባሉ ቦታዎችን አጥር ዛሬ ሲያፈርስ ዋለ። ከመካከላቸው ሚድሮክ የተባለው ድርጅት ተረክቦ ያጠረው እና ለ20 ዓመታት ግንባታ ሳይካሄድበት ቆይቷል የተባለው ፒያሳ የሚገኘው ቦታ አንዱ ነው። የአዲስ አበባ ከንቲባ የፕሬስ ሴክረታርያት ወ/ት ፌቨን ተሾመ ለDW እንዳስረዱት ርምጃው የተወሰደው የአዲስ አበባ ካቢኔ መስከረም 12፣2011 ዓም 154 ቦታዎች ውላቸው ተቋርጦ ለከተማ አስተዳደሩ እንዲመለሱ በወሰነው መሠረት ነው። ወይዘሪት ፌቨንን ኂሩት መለሰ አነጋግራቸዋለች። ከዛሬ 2 ወሩ የአዲስ አበባ አስተዳደር ውሳኔ በኋላ የተከናወኑትን ተግባራት በመዘርዘር ይጀምራሉ።
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ