በአክሱም ሰብዓዊ ቀዉስ ጉዳይ የኢሰመኮ የመጀመርያ ዘገባ
ረቡዕ፣ መጋቢት 15 2013ማስታወቂያ
በአክሱም ከተማ በኤርትራ ወታደሮች ዉስን በሆነ መልኩ በኢትዮጵያ ወታደሮች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈፀሙን ማረጋገጡን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ገለፀ። ኮሚሽኑ ባወጣዉ የመጀመርያ ደረጃ ሪፖርት እና ለዶቼ ቬለ በሰጠዉ ተጨማሪ ማብራርያ ሲቪል ዜጎች ተገድለዋል፤ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ በንብረት ላይ ከፍተኛ ያለዉ ጉዳት ደርሶአል፤ ብሎአል።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ትግራይ ክልል ደረሰ ያለውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እና በሲቪሎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አስመልክቶ የመጀመሪያ ደረጃ (ቀዳሚ) ሪፖርቱን ይፋ አድርጎአል። ኢሰመኮ ዘገባው፦ «ትግራይ ክልል፤ በአክሱም ከተማ የተፈጸመው ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በአጠቃላይ በክልሉ የተሟላ ምርመራ የማድረግን አስፈላጊነት ያመለክታል» ብሏል።
ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ