በአማራ ክልል የተፈናቃዮች ይዞታ
ሐሙስ፣ ጥቅምት 25 2014ማስታወቂያ
በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖች ከምግብ እና ህክምና እጦት ጋር በተያያዘ ለከፋ ችግር መዳረጋቸው እየተነገረ ነው። በክልሉ ህወሓት በያዛቸው አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች በህመምና እና በምግብ እጦት፣ ቡድኖ ወርሮ በለቀቀው የሰሜን ወሎ መቄት ወረዳ ደግሞ የህክምና ቁሳቁሶችና መድኃኒቶች በመዘረፋቸው፣ ከ100 በላይ ሰዎች መሞታቸውን የአማራ ክልል መንግሥት አስታውቋል። የክልሉ የአደጋ መከላከል፤ ምግብ ዋስትና እና ልዩ ድጋሚ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ጉዳዩን የተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።
ዓለምነው መኮንን
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ