1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል የርዕሰ መስተዳድር ለውጥ ላይ የተሰጡ አስተያየቶች

ሰኞ፣ ጥቅምት 30 2013

በአማራ ክልል የተደረገው የርእሰ መስተዳድር ለውጥ አሁን በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሚያስከትለው ተፅእኖ እንደሌለ ምሁራን አመለከቱ፣ አዲሱ ርዕሰ መስተዳድር በተለያዩ የአስተዳደር ኃላፊነቶች ላይ የሰሩ በመሆኑ ክልሉን በብቃት እንደሚመሩት አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል፡፡ 

https://p.dw.com/p/3l3vc
Äthiopien l Agegnehu Teshager - neuer Präsident der Amhara Region
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

በአማራ ክልል የርዕሰ መስተዳድር ለውጥ ላይ የተሰጡ አስተያየቶች

በአማራ ክልል የተደረገው የእርእሰ መስተዳድር ለውጥ አሁን በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሚያስከትለው ተፅእኖ እንደሌለ ምሁራን አመለከቱ፣ አዲሱ ርዕሰ መስተዳድር በተለያዩ የአስተዳደር ኃላፊነቶች ላይ የሰሩ በመሆኑ ክልሉን በብቃት እንደሚመሩት አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል፡፡ 
 የቀድሞውን የአማራ ክልል ርዕሰመስተዳድር የዶ/ር አምባቸው መኮንን መገደል ተከትሎ የአማራ ክልል ምክር ቤት አቶ ተመስገን ጥሩነህን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟቸው ላለፉት 15 ወራት ተኩል ክልሉን ሲመሩ ቆይተዋል፡፡ 
 
ይኸው ምክር ቤት የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩትን አቶ አገኘሁ ተሻገርን አዲስ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል፡፡  አሁን አገሪቱም ሆነ ክልሉ ባሉበት ወቅታዊ ሁኔታ ነባሩን ርዕሰ መስተዳድር አንስቶ አዲስ መሾም አስፈላጊነቱ ምን ያህል ነው ስንል አንዳንድ አስተያት ሰጪዎችን ጠይቀን ነበር፡፡ 
 ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌደራሊዝምና ሰብዐዊ መብት ረዳት ፕሮፌሰር ናቸው፡፡ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ካላቸው ልምድና ሙያ አኳያ ወደ ደህንነት መስሪያ ቤት መዛወራቸው ትክክል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ይህም የደህንነት ስራው ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲከናወን ያደርጋል ብለዋል፡፡ 
 በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር አቶ ቻላቸው ታረቀኝም ቢሆኑ አቶ ተመስገን ወደ ማዕከላዊ መንግስት መሄዳቸው ያለውን ክፍተት ከመሙላት አኳያ ድርሻው የጎላ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ 
 
አዲስ የተሸሙት የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ሰፊ የአስተዳደርም ልምድ ያዳበሩና ክልሉንም በሚገባ የሚያውቁት በመሆኑ ብቃት ያለው አመራር ሊሰጡ እንደሚችሉ በዋና አቃቤ ህግ ማዕረግ የርዕሰ መስተዳድሩ ዋና የህግ አማካሪ አቶ መርሐጽድቅ መኮንን አብራርተዋል፡፡ 
 የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲው የፖለቲካል ሳይንስ መምህሩ አቶ ቻላቸውም ቢሆኑ አዲሱ ርዕሰ መስተዳድር ለክልሉ ትክክለኛ ሰው ናቸው ነው ያሉት፡፡ 
 አቶ ሲሳይ መንግስቴ እንዳሉት አዲሱ ርዕሰ መስተዳድር በክልሉ ውስጥ ለዓመታት የሰሩ በመሆናቸው ሹመቱ ተገቢ ሊሆን እንደሚችል አስረድተዋል፡፡ 

አቶ ተመስገን ጥሩነህ
ምስል DW/A. Mekonnen

ዓለምነው መኮንን

እሸቴ በቀለ
ሸዋዬ ለገሠ