1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል በፊስቱላ የሚጎዱ ሴቶች ቁጥር መጨመር

እሑድ፣ ግንቦት 18 2016

በአገር አቀፍ ደረጃ በፊስቱላ የተጎዱ ሰዎች ቁጥር ወደ 140 ሺህ ያደገ ሲሆን በአማራ ክልል ደግሞ እስከ 39 ሺህ ይደርሳል። 8ኛ ልጃቸውን ሲወልዱ በፊስቱላ የተጠቁ እናት በእውቀት እጥረትና የጤና ተቋማት ሩቅ በመሆናቸው በጤና ጣቢያ መውለድ እንዳልቻሉ ተናግረዋል። በህክምና ክትትል ከፊስቱላ ሊድኑ መቻላቸውን ለዶይቼ ቬሌ ገልጸዋል።፡፡

https://p.dw.com/p/4gFqt
የፊስቱላ ተጠቂ  ከአማራ ክልል
የፊስቱላ ተጠቂ ከአማራ ክልል ምስል Alemnew Mekonnen/DW

በአማራ ክልል በፊስቱላ የሚጎዱ ሴቶች ቁጥር መጨመር

በክልሉ ያለው የፀጥታ ሁኔታና የግንዛቤ ማነስ የፊስቱላ ችግር ያለባቸው ሰዎች ቁጥር መጨመሩን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል። በክልሉ እስከ 39 ሺህ የፊስቱላ ችግር ያለባቸው ሴቶች ይኖራሉ ተብሏል። 7 ልጆችን በቤት ውሰሰጥ የወለደች አንዲት እናት 8ኛ ልጇን ስትወልድ በፊስቱላ መጎዳቷን ጠቅሳ ህክምና ወስዳ ማገገሟን ተናግራለች። የፊስቱላ ቀን በአገር አቀፍ ደረጃ ለ9ነኛ ጊዜ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ12ኛ ጊዜ በባህር ዳር ትናንት ሲከበር የተገኙት በአማራ ክልል ጤና ቢሮ የእናቶች ጤና ክትትል ባለሙያ ዶ/ር ኤርሚያ አዱኛ እንዳሉት በግንዛቤ እጥረትና ክልሉ አሁን ባለበት ወቅታ የፀጥታ ሁኔታ በአማራ ክልልየፊስቱላ ተጠቂ እናቶች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡ የሴትነትን ክብር የሚጻረረው ፊስቱላ

በፊስቱላ የሚጠቁ ሴቶች ቁጥር ጨምሯል


በአገር አቀፍ ደረጃ በችግሩ የተጎዱ ሰዎች ቁጥር ወደ 140 ሺህ ያደገ ሲሆን በአማራ ክልል ደግሞ እስከ 39 ሺህ ይደርሳል ብለዋል፡፡ ሰባት ልጆችን በቤት ውስጥ የወለዱና 8ኛ ልጃቸውን ሲወልዱ በፊስቱላ የተጠቁ እናትእንዳሉት በአለባቸው የእውቀት እጥረትና የጤና ተቋማት በእርቀት ቦታ መገኘት በጤና ጣቢያዎች መውለድ እንዳላስቻላቸው አመልክተዋል፡፡ አሁን ያጋጠማቸውን የፊስቱላ ጤና ችግር በህክምና ክትትል ሊድኑ መቻላቸውን ለዶይቼ ቬሌ ገልጠዋል፡፡ ኖቤል ለፊስቱላ ሆስፒታል መስራቿ

ዶክተር ኤርምያስ አዱኛ ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ
ዶክተር ኤርምያስ አዱኛ ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምስል Alemnew Mekonnen/DW

ሌላ 5 ልጆችን በቤት በተለያዩ ጊዜዎች እንደወለዱ የሚናገሩት እናት በ5ኛው የውልደት ወቅት ለፊስቱላ መጋለጣቸውን ጠቁመው ህመማቸውን አዲስ አበባ ሄደው ታክመው እንደተሻላቸው አመልክተዋል፡፡ በባህር ዳር የሐምሊን ፊስቱላ ማዕከል የህክምና ባለሙያ አቶ ወርቁ ኪሮስ ያለውን ችግር ለማቃለል በጤና ተቋማትና በትምህርት ቤቶች የግንዛቤ ትምህርት ሊሰጥ ገባል ነው ያሉት፡፡ 

የፊስቱላ መንስኤ

ለፊስቱላ በዋናነት የሚያጋልጠው እድያቸው ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ ልጆች እድሜያቸው ሳይደርስ ባል ስለሚያገቡ መሆኑ የፊስቱላ ቀን ታስቦ በዋለበት እለት በውይይቱ ተጠቅሷል፡፡ በቅርቡ የአማራ ክልል ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከ1000 በላይ ያለእድሜ ጋብቻ ጥቆማዎች እንደደረሱት ጠቅሶ ነበር ከነዚህ ውስጥ ደግሞ 130 ያክሉ ጋብቻ መፈፀማቸውን ማረጋገጡን ጠቅሷል፡፡ 

 

ዓለምነው መኮንን 
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ