1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል ምንጃር ወረዳ የሚገኙ ተፈናቃዮች ቅሬታ 

ሐሙስ፣ ነሐሴ 21 2012

ከአንድ ዓመት በፊት ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ተፈናቅለው በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ወረዳ የሚገኙ ተፈናቃዮች አመለከቱ፣ የሁለቱ ክልል የስራ ኃላፊዎች ደግሞ ነዋሪዎቹን ወደ ቀደመው ቀያቸው ለመመለስ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3haMH
Äthiopien | Food aid für Waghemra Zone
ምስል DW/A. Mekonnen

«የእርሻ ማሳችንና መኖሪያ ቤታችንን ተነጥቀን ከአካባቢው ተባርረናል» ተፈናቃዮች

ከአንድ ዓመት በፊት ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ተፈናቅለው በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ወረዳ የሚገኙ ተፈናቃዮች አመለከቱ፣ የሁለቱ ክልል የስራ ኃላፊዎች ደግሞ ነዋሪዎቹን ወደ ቀደመው ቀያቸው ለመመለስ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ ከዛሬ አንድ ዓመት ተኩል በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ተፈጥሮ በነበረው የሰላም መደፍረስ ምክንት አካባቢያቸውን ለቅቀው ወደ አማራ ክልል ሰሜን ሻዋ ዞን ምንጃር ወረዳ አረርቲ ሙያና ቴክኒክ ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች የኦሮሚያም ሆነ የአማራ ክልል መንግስታት ዘላቂ መፍትሔ ሊሰጠን አልቻለም ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡ 
አንዳንድ ተፈናቃዮች ለዶይቼ ቬለ በስልክ እንደነገሩት “የእርሻ ማሳችንና መኖሪያ ቤታችንን ተነጥቀን ከአካባቢው ተባርረናል” ብለዋል፡፡ በመሆኑም ከነቤተሰቦቻቸው በችግር ላይ ስለሚገኙ አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ 
ከተፈናቃዮች አንዷ እንዳሉት በተፈጠረው ችግር ምክንያት ማሳቸውና ቤታቸው በሌሎች ተወስዷል ብለዋል፡፡ በአረርቲ ሙያና ቴክኒክ ተጠልለው ከሚገኙት ተፈናቃዮች መካከል ሌላው ተፈናቃይ እንዳመለከቱት መንግስት አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ባለመቻሉ ከነቤተሰቦቻቸው በችግር ላይ ናቸው፡፡ 
በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረፃዲቅ ተጠይቀው በስጡት ምላሽ ሰዎቹ ወደነበሩበት እንዲመለሱ ከምስራቅ ሸዋ ዞን የመንግስት ኃላፊዎች ጋር እየተነጋገሩበት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ 
 በኦሮሚያ ክልል የምስራቅ ሸዋ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ባይሳ ተመስገን በበኩላቸው በሶስተኛ ወገን ተያዙ የግለሰቦቹ ንብረቶች ነፀ በመሆናቸው ተፈናቃዮች ወደነበሩበት ቢመጡ የሚገጥማቸው ችግር የለም ነው ያሉት፡፡   ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይደገሙ አዋሳኝ የኦሮሚያና የአማራ ክልል አመራሮች በየጊዜው እየተገናኙ ውይይቶችን እንደሚያደርጉ በአማራ የሰሜን ሸዋና በኦሮሚያ የምስራቅ ሸዋ ዞን አመራሮች አመልክተዋል፡፡ 


ዓለምነው መኮንን
አዜብ ታደሰ 
እሸቴ በቀለ