1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በተያዘው አመት ከትግራይ 18 ሺሕ ገደማ ወጣቶች በሕገ-ወጥ መንገድ ስደት ገብተዋል

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 30 2011

ከትግራይ ክልል ባለፈው አንድ አመት ብቻ 18 ሺሕ ገደማ ወጣቶች በሕገ-ወጥ መንገድ ስደት መግባታቸውን የክልሉ ሰራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ። ባለፈው ሐምሌ 18 ቀን ሜድትራኒያን ባሕር ላይ በደረሰ የጀልባ መስጠም አደጋ ከሞቱ ስደተኞች መካከል 16ቱ ከትግራይ ክልል ኢሮብ ወረዳ የተነሱ መሆናቸው ታውቋል።

https://p.dw.com/p/3NSHw
Libysche Migranten ertrunken
ምስል picture-alliance/AP Photo/H. Ahmed

ሜድትራኒያን ከሞቱ ስደተኞች 16ቱ ከኢሮብ ወረዳ የተጓዙ ናቸው

ከትግራይ ክልል ባለፈው አንድ አመት ብቻ 18 ሺሕ ገደማ ወጣቶች በሕገ-ወጥ መንገድ ስደት መግባታቸውን የክልሉ ሰራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ። ሥራ አጥነት፣ የተሳሳተ መረጃ እና የሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ግፊት ዋንኛ ገፊ ምክንያት መሆናቸው ተገልጿል። ባለፈው ሐምሌ 18 ቀን ሜድትራኒያን ባሕር ላይ በደረሰ የጀልባ መስጠም አደጋ ከሞቱ ስደተኞች መካከል 16ቱ ከትግራይ ክልል ኢሮብ ወረዳ የተነሱ መሆናቸው ታውቋል። የሟች ቤተሰቦች ሐዘን ተቀምጠዋል። ከሁለት ሳምንት ገደማ በፊት በደረሰው አደጋ ወደ 150 ገደማ ሰዎች ሳያልቁ እንዳልቀረ ይገመታል።  
ሚሊዮን ኃይለስላሴ 
ኂሩት መለሰ