በትግራይ ጉዳይ የአዉሮጳ ኅብረት አስተያየት
ዓርብ፣ ሰኔ 4 2013ማስታወቂያ
የአዉሮጳ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርዙላ ፎንደርላይን በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሚታየዉ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ በመሆኑ ትኩረት መደረግ አለበት ሲሉ ተናገሩ። ባለድርሻ አካላት በትግራይ ያለዉ ሁኔታ እንዲያዉቁት ለማድረግ ጥሪ ማድረግ ያለብን አሁን ነዉ ብለዋል። ፎንደርላይን ይህን የተናገሩት የበለፀጉት ሃገራት G7 ጉባዔ ላይ ለመገኘት ወደ ኮርንዎል ብሪታንያ ከመጓዛቸው በፊት ነዉ። የኅብረቱ ካዉንስል ፕሬዚደንት ቻርልስ ሚሼልም አብረዋቸዉ ተጉዘዋል። የብረስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ አጠናክሮ ልኮልናል።
ገበያዉ ንጉሴ
አዜብ ታደሰ