1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በትግራይ ይካሄዳል የተባለዉ ምርጫና የተቃዋሚዎች ቅሬታ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 7 2012

በትግራይ ይደረጋል የተባለዉ ምርጫና ለምርጫ ማስፈፀምያ በፀደቁ አዋጆች ዙርያ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተለያዩ ትችቶችን እያቀረቡ ይገኛሉ። አረና ትግራይን ጨምሮ ሌሎች በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በበኩላቸዉ  የክልሉ መንግሥት ከምርጫዉ ሂደት እንዳወጣቸዉ በመጥቀስ ይተቻሉ።

https://p.dw.com/p/3fJ2D
Äthiopien nach TPLF Meeting
ምስል DW/M. Haileselassie

«የክልሉ መንግሥት ከምርጫዉ አዉጥቶናል» የትግራይ ተቃዋሚዎች

በትግራይ ይደረጋል የተባለዉ ምርጫና ለምርጫ ማስፈፀምያ በፀደቁ አዋጆች ዙርያ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተለያዩ ትችቶችን እያቀረቡ ይገኛሉ። ሣልሳዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ የተባለዉ በትግራይ የሚንቀሳቀሰዉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ለምርጫዉ ፍትሃዊነት እና ሕገ-መንግሥታዊነት ያቀረብናቸዉ ሃሳቦች ተቀባይነት ሳያገኙ የምርጫ አዉዱ በክልሉ ምክር ቤት መጽደቁ ተቀባይነቱን ይቀንሰዋል ሲል ገልፆአል። አረና ትግራይን ጨምሮ ሌሎች በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በበኩላቸዉ  የክልሉ መንግሥት ከምርጫዉ ሂደት እንዳወጣቸዉ በመጥቀስ ይተቻሉ።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ