1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በትግራይ ክልላዊ መንግሥት ላይ የተቃዋሚዎች ወቀሳ

ዓርብ፣ የካቲት 20 2012

የትግራይ ክልላዊ መንግስት ለ2332 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉ አስታወቀ፡፡ በይቅርታ እንዲፈቱ ከተወሰነላቸው ታራሚዎች መካከል 25ቱ ኤርትራውያን ናቸው ተብሏል። በሌላ በኩል የትግራይ የሚንቀሳቀሰው ተቃዋሚው የፖለቲካ ድርጅት ዓረና ትግራይ "የታሰሩ አባላቶቼ የይቅርታ ዕድሉ እየተሰጣቸው አይደለም" ብሎ የክልሉ መንግስትን ይወቅሳል።

https://p.dw.com/p/3Yb66
Äthiopien nach TPLF Meeting
ምስል DW/M. Haileselassie

የትግራይ ተቃዋሚ አባላት አሁንም እንደታሰሩ ነዉ

የትግራይ ክልላዊ መንግስት ለ2332 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታወቀ፡፡በይቅርታ እንዲፈቱ ከተወሰነላቸው ታራሚዎች መካከል 25ቱ ኤርትራውያን ናቸው ተብሏል። የትግራይ ክልል ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ሐላፊ አቶ ተኪኡ መተኩ እንደገለፁት 46 ሴቶች የሚገኙባቸው እነዚህ የሕግ ታራሚዎች እንዲፈቱ የተወሰነው በማረሚያ ቤቶች በነበራቸው ቆይታ በሰሩት ወንጀል የተፀፀቱ፣ በቆይታቸው ጥሩ ስነ ምግባር የነበራቸውና ከእስር ወጥተው ማሕበረሰባቸው ይክሳሉ ተብሎ ተስፋ የተደረገባቸው ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በተለያዩ ወንጀል ተፈርዶባቸው እስር ላይ የነበሩ 25 ኤርትራውያን ዜጎችም በይቅርታ እንዲወጡ መወሰኑን የትግራይ ክልል ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ያስታወቀ ሲሆን ይኽም የክልሉ መንግስት ለኤርትራ ህዝብ እያስተላለፈው ያለው የሰላምና ፍቅር ጥሪ ተግባራዊ ማሳያ ብሎታል። በሌላ በኩል የትግራይ የሚንቀሳቀሰው ተቃዋሚው የፖለቲካ ድርጅት ዓረና ትግራይ "የታሰሩ አባላቶቼ የይቅርታ ዕድሉ እየተሰጣቸው አይደለም" ብሎ የክልሉ መንግስትን ይወቅሳል።

 

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ