1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በትግራይ ከ 1 ሚሊዮን በላይ ሕጻናት መማር አልቻሉም ተባለ

ሐሙስ፣ ግንቦት 18 2014

ትግራይ ክልል ውስጥ በጦርነቱ ምክንያት 1 ነጥብ 2 ሚልዮን ህፃናት እና ታዳጊዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ እንደሆኑ ተገለፀ። ከሁለት ዓመት በላይ ከትምህርት ገበታ የራቁ ትግራይ ክልል የሚገኙ ህፃናትና ታዳጊዎች በጦርነቱ ምክንያት «ህልማቸው መደናቀፉ»ን ይናገራሉ።

https://p.dw.com/p/4BtjT
Äthiopien I Mekele Universität
ምስል Million H.Silase/DW

«ከጦርነቱ በፊት ከ1.6 ሚልዮን በላይ ተማሪዎች ትምህርት ላይ ነበሩ»

ትግራይ ክልል ውስጥ በጦርነቱ ምክንያት 1 ነጥብ 2 ሚልዮን ህፃናት እና ታዳጊዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ እንደሆኑ ተገለፀ። ከሁለት ዓመት በላይ ከትምህርት ገበታ የራቁ ትግራይ ክልል የሚገኙ ህፃናትና ታዳጊዎች በጦርነቱ ምክንያት «ህልማቸው መደናቀፉ»ን ይናገራሉ። የትግራይ ክልል፦ ከጦርነቱ በፊት ከ1 ነጥብ 6 ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች በተለያየ ደረጃ በትምህርት ላይ እንደነበሩ ገልጧል። በዚህ ዓመት ግን ትምህርት ከጀመሩ 400 ሺህ ገደማ ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ውጭ ሌሎቹ ለሁለት የትምህርት ዓመታት ወደመማር ማስተማሩ ሒደቱ አልተመለሱም ብሏል። ትምህርት የጀመሩት ህፃናትም ቢሆን ትግራይ ክልል ውስጥ ባለው ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ምክንያት በብዛት ትምህርታቸውን እያቋረጡ ስለመሆኑ በትግራይ ትምህረት ቢሮ የኮምኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ዳኘው አይጠገብ ለዶቼቬለ (DW) ተናግረዋል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሳሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሰ