1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በተመድ የተጠራዉ ለአፍጋኒስታን ለጋሽ ጉባዔ

ሰኞ፣ መስከረም 3 2014

ታሊባን ወደ ስልጣን ከተመለሰ ከአንድ ወር በኋላ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዛሬ ጄኔቫ ስዊዘርላንድ ላይ ለአፍጋኒስታን የለጋሽ ጉባኤ እያካሄደ ነው። በመንግስታቱ ድርጅት ጥላ ስር የተጀመረዉ ጉባዔ በአፍጋኒስታን ረሃብን ለመዋጋት እና የህዝብን ሕይወት ከውድቀት ለማዳን ያለመ ነዉ ተብሎአል።

https://p.dw.com/p/40GjM
Grenze Afghanistan - Pakistan | Flüchtlinge aus Afghanistan
ምስል Saeed Ali Achakzai/REUTERS

ታሊባን ወደ ስልጣን ከተመለሰ ከአንድ ወር በኋላ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዛሬ ጄኔቫ ስዊዘርላንድ ላይ ለአፍጋኒስታን የለጋሽ ጉባኤ እያካሄደ ነው። በመንግስታቱ ድርጅት ጥላ ስር የተጀመረዉ ጉባዔ በአፍጋኒስታን ረሃብን ለመዋጋት እና የህዝብን ሕይወት ከውድቀት ለማዳን ያለመ ነዉ ተብሎአል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች እስከ ታህሳስ ወር ድረስ 606 ሚሊዮን ዶላር (ከ 513 ሚሊዮን ዩሮ) መሰብሰብ እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል። ብዙ አገሮች አፍጋኒስታንን ለመርዳት ዝግጁ ቢሆንም፤ እርዳታዉን ለመስጠት ሁኔታዎች መማላት አለባቸዉ የሚሉ ነጥቦችን ያስቀምጣሉ። በዚህ ጉባኤ የጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃይኮ ማስ ተሳታፊ ናቸዉ።

አዜብ ታደሰ 

እሸቴ በቀለ