1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቦረና ነዋሪዎችን ያሳሰበው ድርቅ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 9 2014

በኢትዮጵያ ዝናብ በሚጠበቅባቸው ባለፉት ወራት ምንም አይነት ዝናብ ባለማግኘታችን ባጋጠመን ድርቅ ከብቶቻቸውን ክፉኛ ተጎድተዋል፤ ሰውም ለርሃብ እየተጋለጠ ነው ይላሉ የቦረና ነዋሪዎች።

https://p.dw.com/p/41rym
BG Dürre | Äthiopien
ምስል picture-alliance/AP Photo/E. Meseret

ድርቅ ያሰጋቸው የቦረና ነዋሪዎች

በኢትዮጵያ ዝናብ በሚጠበቅባቸው ባለፉት ወራት ምንም አይነት ዝናብ ባለማግኘታችን ባጋጠመን ድርቅ ኑሮን የምንመራባቸው ከብቶቻቸውን ክፉኛ ተጎድተው ለችግር ተዳርገናል ይላሉ የቦረና ዞን ነዋሪዎች። ነዋሪዎቹ ከብቶቻችንን ከጥቅም ውጭ እያደረገብን የመጣው ድርቅ አሁን ላይ ሰውንም ወደ ማስራብ ተሸጋግሯል ነው የሚሉት። በቦረና ከዚህ ቀደም የተለያዩ ድጋፎች ይደረጉ እንደነበር ያወሳው የኦሮሚያ ክልል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በቀጣይም በተጨማሪነት በድርቁ ሳቢያ የተጎዱትን ለይቶ ለመርዳት እቅድ መያዙን አውስቷል። ኮሚሽነር አባድር አብዳ በተለይም ለዶይቼ ቬለ እንዳሉት አሁን ላይ በቦረና ድጋፍ የሚሹ ሰዎች ቁጥር ከ600 ሺህ ተሸግሯል።

ስዩም ጌቱ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ