1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቤንሻንጉል የተፈናቃዮች መመለስ

ዓርብ፣ ሰኔ 18 2013

የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ተፈናቃዩች ወደ ቀያቸው ለመመለስ  እየሠራ እንደሚገኝ አስታወቀ። እስካሁንንም ከ16ሺህ በላይ ዜጎች  ወደ  መተከል ተመልሰዋል። ወደ መተከል የተመለሱ ዜጎች በበኩላቸው የሚሰጣቸው እርዳታ በቂ  አለመሆኑን  ገልጸው በቂ ጥበቃ እንዲደረግላቸውም ጠይቀዋል።

https://p.dw.com/p/3vZdo
Äthiopien Vertreibung und Massaker in der Region West-Benishangul Gumuz
ምስል Maria Gerth-Niculescu/DW

«ከ230 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች በክልሉ ይገኛሉ»

የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ተፈናቃዩች ወደ ቀያቸው ለመመለስ  እየሠራ እንደሚገኝ አስታወቀ። እስካሁንንም ከ16ሺህ በላይ ዜጎች  ወደ  መተከል ተመልሰዋል። በቀጣይም እስከ ሰኔ 30/2013 ዓ.ም  50ሺህ ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቀያቸው ለመመስ እየሠሩ እንደሆነ የክልሉ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አቶ ታረቀኝ ተሲሳ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። በመተከል ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ከ230ሺ በላይ ዜጎች በመጠለያ ጣቢያ ያሉ ሲሆን በክልሉ ባጠቃላይ ከ300ሺ በላይ ዜጎች  ደግሞ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑ ተገልጿል። ወደ መተከል የተመለሱ  ዜጎች በበኩላቸው የሚሰጣቸው እርዳታ በቂ  አለመሆኑን  ገልጸው በቂ ጥበቃ እንዲደረግላቸውም ጠይቀዋል። 

በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ከሐምለ 19/2012 ዓ.ም ወዲህ በተለያዩ አካባቢዎች በነበሩ ግጭቶች ምክንያት ከ200ሺ በላይ ዜጎች ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ እንደሚገኙ ከክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡ እነዚህ ተፈናቃዩች አብዛኞቹ በወምበራ፣ቡሌን ድባጢ እና ጉባ እንዲሁም ፓዌ ወረዳ ውስጥ እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡ የኮሚሽኑ ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ታሲሳ በሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋ ተፈናቅሎ በጉባ፣ ቡሌን ድባጢ፣ ወምበራ እና ቻግኒ የነበሩ ዜጎችን ወደ ቀድሞ ቀአቸው ለመመለስ እና በዘላቂነት ለማቋቋም እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ሰሞኑንም ከቻግኒ ከተማ የነበሩ የተወሰኑት ወደ መተከል ዞን  ዳንጉር፣ ቡሌንና ማንዱራ ወረዳዎች መመለሳቸውን ተናግረዋል። በሌላ በኩል በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች በመንግሥት በኩል ይቀርባሉ የተባሉ የዕለት ደራሽ ርዳታዎች በቂ አለመሆናቸውን በተደጋጋሚ ቅሬታ ያቀርባሉ ። የክልሉ አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ሀላፊ አቶ ታረቀኝ ታሲሳ ደግሞ በክልል ለተፈናቃዩች የሚዳረስ እህል ስለመኖሩ ገልጸው በየጊዜ ድጋፍ እያቀረቡ መሆንም አክለዋል፡፡ ከሁለት ወር በፊት የመተከል ዞን የጸጥታ ጉዳይን በበላይነት የሚመራው አስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር ወይም ኮማንድ ፖስት በዞኑ በነበረው የጸጥታ ችግር ወደ ከተማ ከተፈቀናሉ ዜጎች በተጨማሪ ወደ ጫካ በርካቶች መፈናቀላቸውን ገልጸዋል፡፡ ወደ ጫካ ሸሽተው ነበሩ የተባሉ ከ80ሺ በላይ ዜጎችንም ወደ ቤታቸው መመለሱን በወቅቱ አስቸኳይ ጊዜ አስተዳደሩ  አመልክቷል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ 

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ