1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምርጫ ቦርድ ውሳኔና የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየት 

ሐሙስ፣ ጥቅምት 11 2014

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በታህሳስ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምርጫ እንደሚካሄድ አስታውቋል።በክልሉ ከሚንቀሳቀሱት ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ፣በእቅዱ መስማማቱን አስታውቆ የክልሉ ሰላም መሻሻል እንዳለበት አሳስቧል።የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ በበኩሉ ሕግን ከማስከበር ጎን ለጎን ምርጫ መካሄድ አለበት ብሏል፡፡

https://p.dw.com/p/41ytd
Äthiopien Birtukan Mideksa UDJ Partei
ምስል Yohannes Geberegziabher/DW

የምርጫ ቦርድ ውሳኔና የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየት 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በታህሳስ 21/2014 6ኛውን  ምርጫ ለማካሄድ ያስችላል ያለውን ጊዜያዊ  መርሀ ግብር ይፋ አድርጓል፡፡ በቤኒንሻጉል ጉሙዝ በ17 ምርጫ ክልሎች  ምርጫ እንዳልተካሄደ ቦርዱ ትናንት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ገልጸዋል፡፡ ምርጫን አስመልክቶ ከከልል መስተዳድሮችና ጸጥታ አካላት እንዲሁም ከፓርቲዎች ጋር ተከታታይ ምክክሮችን ሲያከናውን መቆየቱንም ቦርዱ አመልክቷል፡፡ ያነጋርናቸው በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ጊዜ ሰለዳ መሰረት ምርጫ መካሄድ አለበት የሚል አቋሚ እንዳላቸውና ዝግጅት እያደረጉ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ምርጫው ከመካሄዱ በፊት በአካባቢው ለሚስተዋለው የሰላም መደፍረስ መንግስት መፍተሄ ሊያበጅ ይገባል ብለዋል፡፡
በመስከረም 20/2014 በቤኒሻንል ጉሙዝ  ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ምርጫ በጸጥታ ችግር ምክንያት ላልተወሰ ጊዜ ተራዝሞ ነበር፡፡ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትናንት ይፋ ባደረገው የጊዜ ሰለዳ መሰረት ደግሞ በታህሳስ ወር ምርጫ በክልሉ እንደሚካሄድ ጠቁመዋል፡፡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሚንቀሳቀሱት ተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ፣ ምርጫ ቦርዱ ባወጣው ጊዜ ሰለዳ መሰረት  መካሄድ አለበት ያሉ ሲሆን የክልሉ የሰላም ጉዳይም መሻሻል እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ አብዱል ሰላም ሸንግል በክልሉ የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግር መቀረፍ እንዳለበት እና ተፎካካሪ ፓርቲዎች ወደ ዞን እና ወረዳዎች በመንቀሳቀስ የምርጫ ቅስቀሳ የሚያደረጉበት ሁኔታ መመቻቸት እንዳለበት አስታውቋል፡፡
ሌላው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚንቀሳቀሰው የቦሮ ዲሞክራቲክ ፓርቲ በበኩሉ በክልሉ የሚገኙ የተፈናቀሉ ዘጎችም በምርጫ የመሳተፍ ዕድል ሊያገኙ ይገባል ብለዋል፡፡ በክልሉ ምርጫ ባልተካደባቸው አካባቢዎች ከዚህ ቀደም ጳጉሜ 1 ለማካሄድ ተወስኖ የነበረ ሲሆን በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት  ለ2ኛ ጊዜ ተራዝመው እንደነበር የፓርቲው የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዩሐንስ ተሰማ ተናግረዋል፡፡ ምርጫውን ሰላማዊ በሆነ መልኩ ለማካሄድ መንግስት በክልሉ ሰላምን ማስፈን እንዳለበትም ጠቁመዋል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ካሚል ሀሚድ በበኩላቸው   በክልሉ ህግን ከማስከበር ጎን ለጎን  በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ መሰረት ምርጫ መካሄድ አለበት የሚል አቋም እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከዚህ ቀደም  ሰነ 14/2013 ዓ.ም በክልሉ  በአሶሳ ዞን  በ302 የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫ ተካሂዶ የነበረ ሲሆን በወቅቱ ተፈጠረ በተባለው የድምፅ መስጫ  ወረቀት እጥረት እና በኮድ ስህተት ምርጫ በተወሰኑ የምርጫ ጣቢያዎች የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ መቋረጡ ይታወሳል፡፡ በዞኑ ከ360ሺ በላይ ዜጎችም የምርጫ ካርድ ወስዶ እንደነበርም በወቅቱ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ገልጾ ነበር፡፡ በክልሉ ብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ ስድስት የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ 

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ