በቤኒ ሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈናቃዮች ወደ ቄዬአቸው የመመለስ ስራ እና የተፈናቃዮቹ ስጋት
ዓርብ፣ ግንቦት 7 2012ማስታወቂያ
የአማራ ክልል እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ኮማንድ ፖስት ተፈናቃዎችን ወደ ቀድሞ ቄአቸው እየመለሰ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ባለፈው ዓመት በመተከል እና ጃዊ አካባቢዎች በነበረው ግጭት ከተፈናቀሉ ዜጎች መካከል እስካሁን 4008 ሰዎች ወደ ቀድሞ ቀያቸው መመለሳቸውን የኮማድ ፖስቱ አባል እና የቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም ግንባታ እና ጸጥታ በሮ ኃላፊ አቶ አበራ ባያታ ተናግረዋል፡፡ ከማንዱራ ወረዳ ተፈናቅለው በአማራ ክልል ጓንጓ ወረዳ የነበሩ 3433 ተፈናቃወዮች ትናንት ወደ ቀያቸአቸው ተመልሰዋል፡፡ 332 የቁም እንስሳት በኮማንድ ፖስቱ ለባለንብረቶች መመለሳቸውን፣ 97 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና ቀስትን ጨምሮ አምስት ሺ(5000) ድምጽ አልባ መሳሪያዎችም መያዛቸውን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
ነጋሳ ደሳለኝ
ታምራት ዲንሳ
አዜብ ታደሰ