1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በባሕር ዳር የደረሱ የሆሮ ጉድሩ ተፈናቃዮች

ሐሙስ፣ መስከረም 19 2015

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ጃረዴጋ ጃርቴና አሙሩ በተባሉ ወረዳዎች ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ምክንያት ባሕር ዳር ከተማ የደረሱ ተፈናቃዮች፤ መንግስት በየዱር ገደሉ ለተበታተኑ ወገኖች እንዲደርስላቸው ተማፀኑ፣ ኦነግ ሸኔ የተባለው ታጣቂ ቡድን ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት ማድረሱንም ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/4HWgI
Äthiopien BahirDar Amhara Zone
ምስል Alemenew Mekonnen/DW

ፈናቃዮቹ፤ መንግስት በየዱር ገደሉ ለተበታተኑ ወገኖች እንዲደርስ እየተማፀኑ ነዉ

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን  ጃረዴጋ ጃርቴና አሙሩ በተባሉ ወረዳዎች ባለፈው ሳምንት በአካባቢው ነበረ በተባለዉ የታጣቂዎች ጥቃት ምክንያት አካባቢዉን ሸሽተው ለማምለጥ የቀናቸዉ ተፈናቃዮች ባሕር ዳር ከተማ መድረሳቸዉ ተነገr። ተፈናቃዮቹ መንግስት ህይወታቸውን ለማትረፍ በየዱር ገደሉ ለተበታተኑ ወገኖች እንዲደርስላቸው ተማጽነዋ፤ አካባቢዉ ላይ ኦነግ ሸኔ የተባለው ታጣቂ ቡድን ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት ማድረሱንም ተፈናቃዮቹ ተናግረዋል፣ የፌደራል ፖሊስና የኦሮሚያ ልዩ ኃይል የተፈጠረውን ችግር ለመከላከል ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸውን መመስከራቸዉም ተነግሯል፡፡

ለውጡን ተከትሎ በበርካታ የኦሮሚያ ክልል በተለይም በአንዳንድ የወለጋ ዞኖች መንግስት ኦነግ ሸኔ ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ኃይል በአማራ ተወላጆች ላይ ጥቃት ሲያደርስ እንደቆየ በተለያዩ ጊዜዎች ከጥቃቱ ያመለጡ ነዋሪዎች ለዶቼ ቬሌ ይገልፃሉ፡፡ በጥቃቱም በርካቶች ተገድለዋል፣ ቆስለዋል፣ ተፈናቅለዋልም፡፡

ባለፈው ሳምንት መስከረም 12/2015 ዓ ም በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ጃረዴጋ ጃርቴና አሙሩ ወረዳዎች ታጣቂዎች በአደረሱት ጥቃት በርካቶች መገደላቸውንና መታፈናቸውን ከጥቃቱ ሸሽተው ባህር ዳር ከተማ የደረሱ ተፈናቃዮች አስረድተዋል፡፡

Äthiopien BahirDar Amhara Zone
ምስል Alemenew Mekonnen/DW

“ የተነሳነው ከጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ አሊቦ ዜሮ 1 ቀበሌ ነው፣ ረቡዕ ማታ ባላሰብነው ጉዳይ ታፍነን ስላደርና ንፁሐን በሙሉ ስለተጎዳብን ከ500 እስከ 600 ነዋሪ በሚኖርበት ቦታ ከዚያ ውስጥ ደግሞ ሉት መውጣትና አለመውጣቱ ሳታወቅ የተወሰኑ እስከ 150 ድረስ ከዚህ የደረሱ አሉ ከዚያ ውጪ ያሉ በህይወት እንደሌሉ ነው እየወሰንን ያለነው፣ በዚያ ላይ ደግሞ ታግተው ያሉ ህዝቦችም ብዙ አሉ፣ ከታገቱት ውጪ ያሉት ደግሞ ሙሉ በሙሉ እንደሌሉ ነው፡፡" ብሏል አንድ ተፈናቃይ፡፡ እስከ 60 የሚሆኑ ሰዎች እንደታገቱ የሚናገሩት ተፈናቃዮቹ፣ መንግስት ለታገቱና በከበባ ውስጥ ለሚገኙ ሰላማዊ ዜጎች እንዲደርስላቸው ጠይቀዋል፡፡

በመንገድ ላይ በውሀ ጥምና በርሀብ የአቅመ ደካሞች ህይወት ማለፉን የሚናገት ተፈናቃዮቹ ቡሬ ምዕራብ ጎጃም ለመድረስ የሶስት ቀን የእግር ጉዞ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፤ በጎዞ ወቅት የፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ ወገናዊ እርዳታ እንዳደረገላቸውም አብራርተዋል፡፡ተፈናቃዮቹ  በህይወት የቀሩ ካሉ መንግስት ጊዜ ሳይወስድ ይድረስካቸው ሲሉም ጠይቀዋል፡፡ ሌላዋ የአሙሩ ወራዳ ተፈናቃይ በጥቃቱ አባታቸውንና  አክስታቸውን እንዳጡ ጠቁመው፣ በመንገድ ላይም ብዙዎች እንደሞቱ አስታውሰዋል፡፡  በአሙሩ ወረዳ በሽዎች የሚቆጠሩ ወገኖች አካባቢያቸውን ለቅቀው በየጫካው የመንግስትን እርዳታ እየፈለጉ እንደሆነ ገልተዋል፡፡

የ9 ቤተሰብ አስተዳዳሪ የነበሩ አንድ አባወራ ችግሩ ሲፈጠር ሁሉም ራሱን ለማትረፍ በየቦታው በመበተኑ የ4 ዓመት ልጃቸውን ጨምሮ ባለቤታቸውና መላው ቤተብ የት እንዳለ እንደማውቁ ገልፀዋል፡፡

“… ህይወታችንን ለማትረፍ ስንሮጥ እኔ ባለ 9 ቤተሰብ ነበርሁ፣ ከ9 ቤተሰብ አንድ ነገር ይዤ ሳልወጣ … ልጆቼ ደግሞ ተበራግገው ከሚስቴ ጋራ 8 ልጆችን ይዛ የት እንደደረሱም አላውቅም፤  ወደ ሁለት ቀበሌ ሚሆን ሰምቡጨፌ ጃወደቦን የሚባሉ አካባቢዎች ህይወታችን እናድን ብለው የወጡ ከ3ሺህ እስከ 5 ሺህ የሚሆን ህዝብ አለ፣ ሌላው በዓባይ ወንዝ ተገድቦባቸው፣ መውጫ በራቸውን ደግሞ በሸኔ ታግተው እስካሁን … እባካችሁ ድረሱልን እለ ሰሚ አጥተው አሁንም ህይወታቸው እዛ ታግቶ  ነው ያለ መንግስት ደርሶ የልጆቸንም፣ የቤተሰቤንም ህይወት እንታደግልኝ እተይቃለሁ፡፡ ልጆቼን፣ ህፃን የ4 ዓመት፣ ከዚያ በላይ ያሉ ህፃን ልጆች ታፍነውብኝ ቀርተዋል ከሚስቴ ጋር፣ አሁን እዚህ ወድቀን ፈስሰን እተሰቃየን እንገኛለን ”

Äthiopien BahirDar Amhara Zone
ምስል Alemenew Mekonnen/DW

ህይወታችን ለመታደግ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል መስዋዕት ከፍሏል የሚሉት ተፈናቃዮቹ  የፌደራል ፖሊስ ከአካባቢው ስንለቅ አጅቦ ወደ ሰላማዊ ቀጠናቆች አድርሶናል ብለዋል፡፡

ፌደራል ፖሊስ ያደረገውን እገዛ በተመለከተ አንድ ተፈናቃይ እንዲህ ብለዋል፣ ” …ፌደራል (ፖሊስ) ደግሞየቻለ የቻለውን እተሸከመ፣ በቁስለኛ ላይ እየደረበ፣ በትክሻው እተሸከመ መሳሪያ እየተሸከመ፣ ልጅ እተሸከመ የወደቀውን እነሳ እንዲህ አድርጎ አጅቦ እኛ ‘ሩሀችንን’ ለማውታት አድርሶናል፡፡”

የስልክ ግንኙነት በጣም አስቸጋሪ ቢሆንም በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ራሱን ደብቆ የሚገኝ አንድ አስተያየት ሰጪ ብዙ ሰው እንደተገደለ፣ አሁንም መከበባቸውን የሚመለክት መረጃ እንዳለው ተናግሯል፡፡

“አሁን እንደተከበብን ነው የምንሰማው፣ ብዙ ህዝብ አልቋል፣ቢያንስ ወደ 500የሚጠጋ እንደዛ አልቋል፡፡”

ዓለምነው መኮንን

አዜብ ታደሰ

ታምራት ዲንሳ