1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በባህርዳር የሰዓት እላፊ ተነሳ 

ዓርብ፣ ጳጉሜን 5 2013

በባህር ዳር ከተማ ከነሐሴ 2013 ዓ ም መጀመሪያ ጀምሮ ለአንድ ወር ያህል ተጥሎ የነበረው የስዓት እላፊ ገደብ መነሳትን ተመልክቶ የምሽት ጭፈራ ቤቶች ወደ መደበኛ ስራዎቸቸው መመለሳቸውን አንዳንድ የባህር ዳር ከተማ ወጣቶች አመለከቱ፣ ወጣቶቹ በጭፈራ ቤቶች እስከ 9 ሰዓት መዝናናታቸውን ገልፀዋል፡፡

https://p.dw.com/p/40Abd
Äthiopien | Bahir Dar
ምስል DW/A. Mekonnen

በአነስተኛ የምሽት ስራ በተሰማሩ ወገኖች ላይ ቻና ፈጥሮ ነበር


በባህር ዳር ከተማ ከነሐሴ 2013 ዓ ም መጀመሪያ ጀምሮ ለአንድ ወር ያህል ተጥሎ የነበረው የስዓት እላፊ ገደብ መነሳትን ተመልክቶ የምሽት ጭፈራ ቤቶች ወደ መደበኛ ስራዎቸቸው መመለሳቸውን አንዳንድ የባህር ዳር ከተማ ወጣቶች አመለከቱ፣ ወጣቶቹ በጭፈራ ቤቶች እስከ 9 ሰዓት መዝናናታቸውን ገልፀዋል፡፡ አንዳንድ የመጠጥ ቤት ባለቤቶች ደግሞ የጦርነቱ ሁኔታ ያለውን ገበያ እንዳቀዛቀዘው ይናገራሉ፣ ዶይቼ ቬለ በከተማዋ ተዘዋውሮ እንዳረጋገጠው እንዳንዶቹ ደግሞ የሰዓት እላፊ ገደቡ ስለመነሳቱ ያልሰሙ ሰዎች አሉ፣ የሰዓት እላፊ ገደቡ በአነስተኛ የምሽት ስራ በሚሰሩ ወገኖች ላይ የኢኮኖሚ ጫና ፈጥሮ እንደነነበርም ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ተጠባባቂ ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ገደቡ የተነሳበትን ምክንያት ለዶይቼ ቬለ ተናግረው ነበር፡፡ ከንቲባው የሰዓት እላፊ ገደቡ የተነሳበትን ምክንያት በማስቀደም የነዋሪዎችን አስተያየት እንደሚከተለው ይቀርባል።


ዓለምነው መኮንን
አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ