1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

Merga Yonas Bula
ረቡዕ፣ መስከረም 17 2010

በሶማልያ መንግሥት አንፃር የሚዋጋው የአሸባብ ሚልሺያ ቡድን በ2003 ዓ/ም ከዋና ከተማ ከሞቃድሾ ተገፍቶ ቢወጣም በፈንጂ የሚጥላቸውን ጥቃቶችና ግድያዎች አለቋረጠም። በጎረቤት አገር ኬንያም  ላይ አልፎ አልፎ የሽብር ጥቃት ፈጽሟል።

https://p.dw.com/p/2kpbY
Somalia Al-Shabaab Kämpfer
ምስል picture alliance/AP Photo/F. A. Warsameh

Somalia's State Building, Anti-Terror Fight - MP3-Stereo

በ22,000 ጠንካራ የአፍሪቃ ህብረት ጓድ የሚረዳው የሶማሊያ ጦር ሰራዊት እና የአሜሪካ አብራሪ የለሽ የጦር አዉሮፕላን ከቅርብ ወራቶች ወዲህ  በአሸባብ አንፃር ጥቃታቸውን አጠናክረዋል።

የአሜሪካ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በአልሸባብ ላይ ጠንካራ ወታደራዊ ርምጃ  እንዲወሰድ ካዘዙ ስድስት ወራት ሆኗል። ሰዎች ከብዙ ጊዜ አንስተው በድርቅ በመሰቃየት ላይ በሚገኙባቸው አክራሪው አሸባብ በሚቆጣጠራቸዉ አካባቢዎች አሁን ዩኤስ አሜሪካ የምታካሂደው ጥቃት ብዙ እያነጋገረ ነው። ምክንያቱም አሜሪካና ሶማሊያ በአሸባብ አንፃር በጋራ በጀመሩት ጥቃት ብዙ ሲቭሎች ተገድለዋል፣ ይህም አስቸኳይ ርዳታ በሚያቀርቡ ወገኖች ስራ ላይ እክል ደቅኗል በሚል ከርዳታ ሰጪዎቹ በኩል ብርቱ ወቀሳ አሰንዝሯል።

በጦርነቱ ሚክንያት የተፈናቀሉ 600ሽ የሚሆኑ ሶማሊያዉያን ከሞቃድሾ ወጣ ብሎ በሚገኘው ባድባዶ በተባለው የስድተኞች መጠለያ ጣቢያ ይኖራሉ። በዚህ ጣቢያ ግን ምግብና ዉሃ ማግኘት ይከብዳል። የአንድ ልጅ እናት የሆነችዉ ፋጥማ ከሁለት ሳምንት በፊት ነዉ ወደ ካምፑ የመጡት። ሁለቱም ርዳታ እየተጠባበቁ ይገኛሉ። አሸባባ በተቆጣጠራቸዉ ሰፈር በረሃብ ከመሞት የካምፑ ህይወት እንደሚሻል ፋጥማ ትናገራለች።

Dürre Hungersnot Afrika Flash-Galerie
ምስል picture alliance/dpa

«አሸባብ ፣ ከሀይማኖት የለሽ ርዳታ ከምንቀበል ብንሞት ይመርጣል፣» ስትል ፋጥማ ትናገራለች።

ሁሉም ሶማሌዎች ግን አይደሉም ከረሃብና ከአሸባብ የሚሸሹት። ጥቂት  ራቅ ብሎ ሌላ የስድተኞች ካምፕ ይገኛል። ማርያን ከሞቃድሾ 60 ኪሎሜትር ርቃ ከምትገኘው ባርሬ ተሰዳ በዝህ ካምፕ ትገኛለች። ከአንድ ወር በፊት የሶማሊያና የአሜርካ ወታደሮች በፈፀሙት ጥቃት ከ10 ያላነሱ ሲቭሎች ተገድለዋል። የማርያ ባል ከተገደሉት አንዱ ነበር።

«ዉጊያ ለኛ የተለመደ ነገር ነው። ይሁንና፣ ይህ እስካሁን ካየነው ሁሉ እጅግ የከፋው ነው፣» ስትል ማርያን ያለዉን ሁኔታ ትናገራለች።

በመጋቢት ወር የአሜረካ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በአሸባብ ላይ የሚደረገዉ ጦርነት በልዩ ወታደራዊ ሃይል እንዲጠናከር አዘዋል።አሸባብ ባለፈዉ ዓመት ከ4200 ሰዎች በላይ ገድሎዋል።

ከጥር ወር ወዲህ በሞቃድሾ የተመሰረተው አዲሱ መንግስት የአለም አቀፍ እገዛ ያገኛል። ይሁን እንጅ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በአሜሪካ አብራሪ የለሽ የጦር አዉሮፕላን በመደገፍ በአሸባብ ላይ በጀመረው ዘመቻ  ሲቭሉን ህዝብ አደጋ ላይ እየጣለ ነው በሚል ይወቀሳል። አንድ የቀድሞዉ የአሸባብ አባል ጥቃት በሚካሄድበት አከባቢብ የሚኖሩ ሰዎች የመንግስትንም ወታዳሮችን ልክ እንደ አሸባብ እንደሚፈሩ ገልጿል።

AMISOM - Soldaten in Somalia
ምስል picture alliance/AP Photo/Jones

«ሰዎቹ መንግስትን አያምኑም። አሸባብ ሲቆጣጠራቸዉ በነበሩት ቦታዎች የሚኖሩ ሰዎች በመንግሥት ጦር ዝርፊያና አስገድዶ መድፈር ተግባር እንዳይፈጸምባቸው ይፈራሉ። አሸባብም ይህንኑ የሰዎቹን ፍራቻ ለራሱ ጥቅም ላይ እያዋለ ነው፣» ስል የቀድመዉ የአሸባብ አባል የነበረዉ ግለሰብ ይናገራል።

በተባባሩት መንግስት የሶማልያ ልዩ ልዑክ ሚካኤል ኬትንግ የሶማልያ ውዝግብ በወታደራዊ ርምጃ እንደማይፈታ ያምናሉ። የዩኤስ አሜሪካ ጣልቃ ገብነትን ቢቀበሉም፣ የአሜሪካ ዋና ትኩረት መንግሥቱን ማጠናከር መሆን እንደሚገባው ገልጸዋል። በአሁኑ ጊዜ ከቦታቸዉ የተፈናቀሉ ሶማሌዎች በየቀኑ ሞቃድሾ ከተማ ይገባሉ። ሰባት ሚልዮን ብሎም ግማሹ የአገሪቱ ሕዝብ በአስቸኳይ ርዳታ ላይ ጥገኛ ሆኖዋል።

ዛንድራ ፕቴርስማን

መርጋ ዮናስ

አርያም ተክሌ