በሲዳማ ዞን ግጭት ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ
ሐሙስ፣ ሐምሌ 25 2011ማስታወቂያ
የመርማሪ ፖሊስ ግለሰቦቹን በሀዋሳ ከተማና በሲዳማ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ከሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት በተከሰቱ ሁከቶች ለጠፋው የሰው ሕይወትና ንብረት ጠርጥሪያቸዋለሁ ሲል ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል። ተጠርጣሪዎቹ በበኩላቸው ጉዳያቸው ከሕግ ይልቅ ፖለቲካዊ ይዘት ያለውና ምንአልባትም በበላይ ኃላፊዎች ትዕዛዝ የተፈጸመ ነው የሚል እምነት እንዳላቸው ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል። የችሎቱን ውሎ የተከታተለው የሐዋሳው ወኪላችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ ተጨማሪ ዘገባ ልኮልናል።
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ሸዋዬ ለገሠ
እሸቴ በቀለ