በሰኔ 15ቱ ግድያ የተጠረጠሩ የክስ መከላከያ አሰሙ
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 1 2012ማስታወቂያ
ባለፈው ዓመት ሰኔ 15 ቀን በአማራ ክልል ተሞከረ ከተባለው መፈንቅለ መንግሥት እንዲሁም በአዲስ አበባ በከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣናት ላይ በተፈፀመው ግድያ ጋር በተያያዘ የተከሰሱ 13 ተጠርጣሪዎች በዛሬው ዕለት የክስ መቃወሚያቸውን አቀረቡ። የክስ መከላከያ ካቀረቡት መካከል በቀድሞዉ የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም በጀነራል ሰዓረ መኮንን ገዳይነት የተጠረጠረው የአስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ እና የአብን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ ይገኝባቸዋል። ተከሳሾቹ የክስ መቃወሚያቸውን ያቀረቡት ለፌደራል የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ላይ የሚፈፀም ወንጀል አንደኛ ችሎት መሆኑን ከአዲስ አበባ ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የላከልን አጭር ዘገባ ያመለክታል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ