በሰሜን ኢትዮጵያ እየተስተጓጎለ ላለው የዕርዳታ ተደራሽነት የመንግስት ምላሽ
ቅዳሜ፣ ጥር 14 2014ማስታወቂያ
በትግራይ ለሚስተዋለው ሰብዓዊ ቀውስ እና የእርዳታ ቁሳቁሶች እጥረት ዋነኛ ተጠያቂው በሰሜን ኢትዮጵያ መንግስትን የሚፋለመው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መሆኑን የኢትዮጵያ መንግስት አስታወቀ፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) በሳምንቱ መጨረሻ ባወጣው ሳምንታዊ ሪፖርቱ በጦርነት ለተጎዳዉ የትግራይ ሕዝብ የሚሰጠዉ የአስቸኳይ ጊዜ ርዳታ እየተሟጠጠ መሆኑን አስታወቋል።
አስተያየታቸውን ለዶይቸ ቬለ የሰጡት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ መንግስት የእርዳታ ቁሳቁሶች ወደ ትግራይ እንዲገቡ ከረጂ ተቋማት ጋር ብርቱ ጥረቶችን እያደረገ ቢሆንም ህወሓት ግጭት በማስነሳት የእርዳታ ማስተላለፊያ መንገዶችን እንደሚዘጋ ገልጸዋል፡፡
ስዩም ጌቱ
ታምራት ዲንሳ