1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ የትግራይ ተወላጆች መፈናቀል

ሐሙስ፣ መጋቢት 2 2013

ሱዳንን እና ኤርትራን ከሚያዋስነው ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ በርካታ የትግራይ ተወላጆች መፈናቀላቸውን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ዐስታውቋል። ከትናንት በስትያ 46 መኪኖች ላይ የተጫኑ ተፈናቃዮች ወደ ትግራይ መግባታቸውን ጊዜያዊ አስተዳደሩ ገልጧል።

https://p.dw.com/p/3qVD9
Karte Ethiopia und Eritrea ENG

ተፈናቃዮቹ በትግራይ የተለያዩ ቦታዎች ይገኛሉ ተብሏል

ሱዳንን እና ኤርትራን ከሚያዋስነው ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ በርካታ የትግራይ ተወላጆች መፈናቀላቸውን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ዐስታውቋል። ከትናንት በስትያ 46 መኪኖች ላይ የተጫኑ ተፈናቃዮች ወደ ትግራይ መግባታቸውን ጊዜያዊ አስተዳደሩ ገልጧል። ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) አካባቢውን ይቆጣጠር በነበረበት ያለፉት ሦስት ዐሥርተ ዓመታት ግድም በርካታ የአማራ ተወላጆች ከአካባቢው ስልታዊ በሆነ መንገድ ሲፈናቀሉ እና ሲገደሉ እንደነበር ቀደም ሲል በተደጋጋሚ ሲዘገብ ነበር። የአማራ ክልል ቦታው ቀደም ሲል በሕወሓት በኃይል ተነጥቆ የነበረ እና አሁን ወደ ቀድሞ ይዞታው መመለሱን ይናገራል። የአማራ ክልል ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ ትግራይ ዉስጥ ደረሰ በተባለ ግድያና ግፍ ተሳትፏል መባሉን የአማራ ክልል አስተባብሏል። የአማራ ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ ግዛቸዉ ሙሉነሕ ዛሬ ለአዣንስ ፍራንስ ፍራንስ ፕሬስ በሰጡት መግለጫ አቶ ግዛቸዉ አክለዉ የአማራ ኃይል የሠፈረበት ግዛት አሁን የአማራ ሆኗል፤ በታሪክም የትግራይ ሳይሆን «የአማራ ነዉ።» ማለታቸዉን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ጠቅሷል። ግዛቱን ግን ዘገባዉ አልጠቀሰም።
ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ