በሞጣ ከተማ ጥቃት ለተቃጠሉ መስጊዶች ርዳታ
ዓርብ፣ ጥር 22 2012ማስታወቂያ
ዛሬ በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች በሞጣ ከተማ ጥቃት ለተቃጠሉ መስጊዶችና የንግድ መደብሮች ማሠሪያ የገንዘብ ማሰባሰብ እንቅስቃሴተከናውኗል። ለዚህ ተግባር ሕዝበ ሙስሊሙ ድጋፍ እንዲያደርግ በሚል ጥሪ ተደርጎ የቆየ ሲሆን፤ ሕዝቡ ከስግደቱ ጎን ለጎን ገንዘብ በመለገስ ድጋፉን አሳይቷል። የአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ሰለሞን ሙጬ በትልልቆቹ የፒያሳው ኑር መስጊድ እና የፍል ውኃው ቶፊቅ መስጊዶች የገንዘብ ማሰባሰብ ተግባሩን ተመልክቷል። በገቢ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብሩ ላይ ክርስትያን ወገኖችም ድጋፍ ሲያደርጉ እንደነበር ተገልጧል። ወጣቶች «ለሞጣ» የሚሉ ጽሑፎች የተለጠፉባቸው ካርቶኖችን ይዘው ገንዘብ ሲሰበስቡም ተመልክቷል።
ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ