1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

28 ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ 

ረቡዕ፣ መጋቢት 22 2013

በዚህ ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥርም ከዚህ በላይ ሊጨምር እንደሚችል ዶቼቬለ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ጋምቤል በተባለ ወረዳ ንጹሐን ዜጎች በታጣቂዎች መገደላቸውን ዛሬ ጠዋት በማሀበራዊ ድረ ገጹ ባወጣው  መግለጫው አስታውቋል። መግለጫው የጉዳቱን መጠን ግን አልገለጸም፡፡

https://p.dw.com/p/3rRfr
Karte Äthiopien englisch

28 ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ 

በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ጋንበል ወረዳ ቦኔ በተባለች ቀበሌ ውስጥ 28 ዜጎች በታጣቂዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለDW  ተናግረዋል፡፡ በወረዳው ትናንት ማምሻውን ደረሰ በተባለው በዚህ ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥርም ከዚህ በላይ ሊጨምር እንደሚችል ዶቼቬለ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምእራብ ወለጋ ዞን ባቦ ጋምቤል በተባለ ወረዳ ንጹሐን ዜጎች በታጣቂዎች መገደላቸውን ዛሬ ጠዋት በማሀበራዊ ድረ ገጹ ባወጣው  መግለጫው አስታውቋል፡፡  ንጹን ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገዳላቸውን ያብራራው መግለጫው የጉዳት መጠኑን ግን አልገለጸም፡፡ በጥቃት አድራሾች ላይ እርምጃ ስለመወሰዱም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡የአሶሳው ወኪላችን ነጋሳ ደሳለኝ ከክልሉ እና የዞን የስራ ሀላፊዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በስልክ ያደረከው ጥረት ስልካቸው ባለመስራቱ አልተሳካም፡፡ነጋሳ ዝርዝሩን ልኮልናል 
ነጋሳ ደሳለኝ 
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ