1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በመንግስት እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የሰላም ድርድር የተፈናቃዮች ተስፋ

ቅዳሜ፣ ኅዳር 1 2016

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ጊዜያት በተፈጠሩ ግጭቶች ተፈናቅለው በየመጠለያ ጣቢያ እና በተለያዩ አከባቢ ያሉ ተፈናቃዮች የኢትዮጵያ መንግስት እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በተለምዶ (ኦነግ ሸኔ) በታንዛንያ ዳሬሰላም እያካሄዱ ያሉት ድርድር ተስፋ ሰጪ ነው ይላሉ፡፡

https://p.dw.com/p/4YhMt
ከወለጋ ተፈናቅለው ጎጅም ውስጥ የሚገኙ የአማራ ብሄር አባላት
የወለጋ ተፈናቃዮች በ,ሰላም ድርድሩ ተስፋ አድርገዋል። ምስል Alemnew Mekonnen/DW

በመንግስት እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የሰላም ድርድር  የተፈናቃዮች ተስፋ

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ጊዜያት በተፈጠሩ ግጭቶች ተፈናቅለው በየመጠለያ ጣቢያ እና በተለያዩ አከባቢ ያሉ ተፈናቃዮች የኢትዮጵያ መንግስት እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በተለምዶ (ኦነግ ሸኔ) በታንዛንያ ዳሬሰላም እያካሄዱ ያሉት ድርድር ተስፋ ሰጪ ነው ይላሉ፡፡የወለጋ ተፈናቃዮች ሮሮ

በሰላም እጦቱ ብዙ ነገር ካፈራንበት ቀዬ ተፈናቅለናል የሚሉት አስተያየት ሰጪዎቹ ዘላቂ ሰላም የሚሰፍን ከሆነ ወደ ነባሩ ቀዬያቸው ተመልሰው የተረጋጋ ህይወት የመምራት ተስፋቸውንም ያጋራሉ፡፡

ከወለጋ ተፈናቅለው በአማራ ክልል መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ የአማራ ብሔር አባላት
በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ጊዜያት በተፈጠሩ ግጭቶች ተፈናቅለው በየመጠለያ ጣቢያ እና በተለያዩ አከባቢ ያሉ ተፈናቃዮች የኢትዮጵያ መንግስት እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በተለምዶ (ኦነግ ሸኔ) በታንዛንያ ዳሬሰላም እያካሄዱ ያሉት ድርድር ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል።ምስል Alemnew Mekonnen/DW

ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ከተለያዩ  ወረዳዎች ተፈናቅለው በዚያው አከባቢ እንዲሁም በሰሜን ወሎ ጃራ የተፈናቃዮች ካምፕ እንዲሁም ደቡብ ወሎ ቃሉ የተፈናቃዮች ካምፕ የተጠለሉትና አስተያየታቸውን ያጋሩን ተፈናቃዮቹ በድርድሩ ሰላም የሚሰፍን ከሆነ ወደ ተረጋጋ ህይወት በመመለስ ኑሮያቸውን ለመምራት መደላድል እንደሚፈጥርም ይተማመናሉ፡፡የወለጋው ግጭት ያፈናቀላቸው ወገኖች የእርዳታ ጥሪ

ተፈናቃዮቹ በሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች መካከል የሚደረገው ድርድር ግን ለአጠቃላ ህብረተሰብ የውይይት መድረኮች አዘጋጅቶ ዘላቂ ሰላም ማስፈን የሚችልና ለዚያም መደላድል የሚፈጥር መሆን ይገባል ይላሉ፡፡ በዚሁ አስተያየታቸውም ከታች የመንግስት መዋቅር ጀምሮ በመፈተሽ ለሰላሙ መደፈርስ መጠየቅ ያለብትም አካል እንዲጠየቅ ተፈናቃዮቹ ወትውተዋል፡፡
የተፋላሚዎቹ ችግሮችን በሰላም መፍታት ተፈናቃዮቹን ወደ መደበኛ ህይወታቸው እንደሚመልስም ተስፋው ሰፊ ነው፡፡

ስዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ