1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በመቀሌ ከተማ ለአራተኛ ቀን የአየር ጥቃት መፈጸሙ

ዓርብ፣ ጥቅምት 12 2014

የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል በሳምንት ውስጥ ለአራተኛ ጊዜ የአየር ጥቃት ፈጽሟል። ጥቃቱ በህወሓት የወታደራዊ ተቋም ላይ ያነጣጠረ እንደነበር የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል። የዛሬው ጥቃት  በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ አሪድ ካምፓስ አካባቢ መፈጸሙን የዶይቼ ቬሌው ዘጋቢ ሚሊዮን ኃይለስላሴ አረጋግጧል።

https://p.dw.com/p/421gn
Äthiopien | Erneuter Luftangriff auf Hauptstadt von Tigray
ምስል AP Photo/picture alliance

ለአራተኛ ቀን በመቀሌ የተፈጸመው የአየር ጥቃት

የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል በሳምንት ውስጥ ለአራተኛ ጊዜ የአየር ጥቃት ፈጽሟል። ጥቃቱ የሕወሓት ኃይሎች የሚገለገሉበት የወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም ላይ ያነጣጠረ እንደነበር የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት በማሕበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። ጥቃቱ መፈጸሙን የሕወሓት ቃል አቃባይ ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል። የዛሬው ጥቃት በመቀሌ ከተማ ደቡባዊ አቅጣጫ  በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ አሪድ ካምፓስ አካባቢ መፈጸሙን የዶይቼ ቬሌው ዘጋቢ ሚሊዮን ኃይለስላሴ አረጋግጧል። በጥቃቱ በሰዎች ላይ  ጉዳት ስለመድረሱ የተባለ ነገር የለም።  የዛሬውን ጥቃት ጨምሮ የሰሞኑን የአየር ጥቃት በተመለከተ ስለደረሰው ጉዳት እና ተያያዥ ጉዳዮች ነጋሽ መሀመድ ሚሊዮንን በስልክ አግኝቶ አነጋግሮታል።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ 

ነጋሽ መሐመድ

ታምራት ዲንሳ