በመረጃ ፍሰቱ ላይ የሚታየው ክፍተት
እሑድ፣ ሐምሌ 25 2013ማስታወቂያ
ካለፈው ጥቅምት ወር መጨረሻ አንስቶ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚነገረው ጦርና የጦርነት ወሬ ብቻ መስሏል። እንዲህ ያለው ስጋት ባጠላበት ወቅት ዜጎች ተገቢና የተጣራ መረጃ እንዲያገኙ የማረግ ኃላፊነት የመንግሥት ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በዚህ ረገድ የመረጃ ክፍተት መኖሩ ጥቂት የማይባለው የኅብረተሰብ ክፍል ዘመን ያመጣለትን ስልት ተጠቅሞ ያልተጣሩ ወሬዎች ወደሚናፈሱባቸው የማኅበራዊ ትስስር ዘዴዎች ትኩረቱን እንዲያደርግ አስገድዷል። በዚህ ደግሞ ያልተጣሩ ሀገራዊ ጉዳዮች መናፈሳቸው ኅብረተሰቡ የደህንነት ስጋት እንዲሰማው ማድረጉን ታዛቢዎች ይናገሩታል። ጉዳዩ የሀገር እና የዜጎች የደህንነት ጉዳይ እንደመሆኑም የተቀናጀ እና የሰከነ የመረጃ ፍሰት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በዚህ ወቅት አስፈላጊ መሆኑን ይመክራሉ። በመረጃ ፍሰቱ ላይ የሚታየው ክፍተት እና ተጠያቂትን የቃኘ ውይይት ዶቼ ቬለ አካሂዷል፣ በውይይቱ ከተነሱት ነጥቦች የሚከተሉት ይገኙበታል።
ሸዋዬ ለገሠ