1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በ 20ዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች በሜድትራኒያን ባሕር ሳይሞቱ አልቀረም ተባለ

ማክሰኞ፣ መስከረም 5 2013

በሜዲትራኒያን ባህር ስደተኞችን አሳፍራ ከሊቢያ የተነሳች የፕላስቲክ ጀልባ በሜዲትራኒያን ባህር ውስጥ ሰጥማ በሃያዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ አለማቀፉ የፍልሰተኞች ጉዳይ ድርጅት (IOM) አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/3iVl6
Seenotrettung Mittelmeer
ምስል AFP/P. Barrena

በሜዲትራኒያን ባህር ስደተኞችን አሳፍራ ከሊቢያ የተነሳች የፕላስቲክ ጀልባ በሜዲትራኒያን ባህር ውስጥ ሰጥማ በሃያዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ አለማቀፉ የፍልሰተኞች ጉዳይ ድርጅት (IOM) አስታወቀ። ከሊቢያ የባህር ዳርቻብዙም ሳትርቅ  በሰጠመችው ጀልባ ላይ ከተሳፈሩት ስደተኞች ውስጥ አብዛኞቹ ግብጻዊያን ሳይሆኑ እንዳልቀረ ተገልጿል። ከአደጋው በኋላ የሁለት ሰዎችን አስክሬን ሲገኝ የተቀሩት 22 ሰዎች አሁንም ድረስ የት እንደደረሱ አለመታወቁን  የአለማቀፉ የፍልሰተኞች ጉዳይ ድርጅት (IOM) ቃል አቃባይ ሳፋ ምሴህሊ ከጄኔቫ በሰጡት መግለጫ አስታውቃዋል። ጀልባዋ ባለፈው እሁድ ከወደብ ከተማዋ ባውያ የግብጽ እና የሞሮኮ ዜግነት ያላቸውን ስደተኞች አሳፍረው ጉዞ ከጀመሩ ሶስት ጀልባዎች አንዷ መሆኗ ታውቋል። የሊቢያ የጠረፍ ጠባቂዎች ከአደጋው የተረፉ 45 ሰዎችን ትናንት ሰኞ ምሽት ወደ ትሪፖሊ መመለሳቸውን የጀርመን ዜና ምንጭ  (dpa) ዘግቧል።  የዓለማቀፉ የፍልሰተኞች ጉዳይ ድርጅት (IOM) እንዳለው ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ ደቡባዊ  አውሮጳ ለመድረስ ጉዞ የጀመሩ 400 ያህል ፍልሰተኞች በማዕከላዊ የሜዲትራንያን ባህር ሰጥመው ሞተዋል።

 

ታምራት ዲንሳ 

አዜብ ታደሰ