1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቅሬታ በቦይንግ ማክስ 8 አውሮፕላን ወደሥራ መመለስ

ረቡዕ፣ መስከረም 5 2014

በኢትዮጵያ የተከሰከሰውና ታግዶ የቆየው ቦይንግ መራሹ ማክስ 8 አውሮኘላን እንደገና የበረራ ፈቃድ ማግኘቱ በአደጋው ተጎጂ ቤተሰቦች ዘንድ ቁጣ መቀስቀሱን ዶይቸ ቨለ ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያ ዐስታወቁ።

https://p.dw.com/p/40MMh
Gedenkfeier für die Toten der abgestürzten Boing 737 -8 max Ethiopian Airlines
ምስል DW/S. Muchie

ወደሥራ ለመመለስ መዘጋጀቱ የተጎጂ ቤተሠቦችን አሳዝኗል

በኢትዮጵያ የተከሰከሰውና ታግዶ የቆየው ቦይንግ መራሹ ማክስ 8 አውሮኘላን እንደገና የበረራ ፈቃድ ማግኘቱ በአደጋው ተጎጂ ቤተሰቦች ዘንድ ቁጣ መቀስቀሱን ዶይቸ ቨለ ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያ ዐስታወቁ። በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡ ቤተሰቦችን በመወከል ጥብቅና የቆሙት አቶ ሼክስፒር ፈይሳ እንደገለፁት አውሮኘላኑ እንደገና ወደሥራ ለመመለስ መዘጋጀቱ የተጎጂ ቤተሠቦችን አሳዝኗል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ያደረገው ስምምነትም ተገቢ አለመሆኑን አቶ ሼክስፒር አመልክተዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስለጉዳዩ ከዶይቸ ቨለ ለቀረበለት ጥያቄ በሰጠው ምላሽ በአውሮኘላኑ ዲዛይን ላይ የተለያዩ ማሻሻያዎች ከተደረጉ በኋላ ደኅንነቱ አስተማማኝ መሆኑን አምነንበታል ብሏል።

ታሪኩ ኃይሉ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ