1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስፔንን ቀዉስ ዉስጥ የጣለዉ የመገንጠል ጥያቄ

ሰኞ፣ ጥቅምት 20 2010

ከ3 ሳምንት በፊት በስፔን ማዕከላዊ መንግስት እና በራስ ገዟ የካታላን አስተዳደር የተፈጠረዉ ዉዝግብ እና ሕገ መንግሥታዊ ቀዉስ በዚህ ሳምንት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። ልክ የዛሬ ወር የግዛቲቱ መንግሥት ያካሄደዉንና አብዛኛዉ ሕዝብም ነፃነት መረጠ የተባለበትን ሕዝበ ዉሳኔ ማዕከላዊዉ መንግሥት ሕገ ወጥ ነዉ በማለት ያገደዉ መሆኑ የሚታወስ ነዉ።

https://p.dw.com/p/2ml6J
Spanien - Demonstrationen für die Einheit von Spanien und Katalonien in Barcelona
ምስል Reuters/Y. Herman

የካታላን መገንጠል አቀንቃኞችን የሚቃወም ሕዝብም አለ፤

የግዛቲቱ ፓርላማ ግን ባለፈዉ ዓርብ የምርጫዉን ዉጤት መሠረት አድርጎ የግዛቲቱን ነፃነት አዉጇል። የስፔን መንግሥትም የግዛቲቱን ባለስልጣኖች በመሻር በዛሬዉ ዕለት ክስ እንደሚመሠርትባቸዉ አስታዉቋል። የመገንጠል አቀንቃኝ የሆኑት የካታላን ባለስልጣናት ግን ለማድሪድ ትዕዛዝ ሆነ ማሳሰቢያ ቁብ የሰጡ አይመስሉም። ገበያዉ ንጉሤ ከብራስልስ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ