1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስደተኞችን የማንሳት ዘመቻ በፓሪስ

ሐሙስ፣ ግንቦት 23 2010

አብዛኛዎቹ የሱዳን የኤርትራ እና የኢትዮጵያ እንዲሁም የአፍጋኒስታን ስደተኞች መሆናቸው ተነግሯል። ተገን ጠያቂ ስደተኞቹ በትናንሽ ድንኳኖች ተጠልለው ይኖሩባቸው ከነበሩት ከነዚህ ስፍራዎች በመነሳታቸው ተደስተዋል።

https://p.dw.com/p/2yjWg
Frankreich Polizei räumt Migranten-Zeltlager in Paris
ምስል Getty Images/AFP/G. Julien

ስደተኞችን የማንሳት ዘመቻ በፓሪስ


በፓሪስ ጎዳናዎች እና በወንዞች ዳርቻ ሰፍረው ከሚገኙት ቁጥራቸው ወደ  3 ሺህ ይጠጋል ከተባሉ ስደተኞች መካከል ትናንት 1 ሺህ ያህሉን ፖሊስ አስነስቷል። እነዚሁ ስደተኞች በጊዜያዊነት በተዘጋጀላቸው የስፖርት ማዘውተሪያ ጅምናዚየሞች ነው የተወሰዱት። ከመካከላቸው አብዛኛዎቹ የሱዳን የኤርትራ እና የኢትዮጵያ እንዲሁም የአፍጋኒስታን ስደተኞች መሆናቸው ተነግሯል። ተገን ጠያቂ ስደተኞቹ በትናንሽ ድንኳኖች ተጠልለው ይኖሩባቸው ከነበሩት ከነዚህ ስፍራዎች በመነሳታቸው ተደስተዋል። የፓሪስ ከተማ ባለሥልጣናትም ስደተኞቹን ማንሳቱ በመሳካቱ ረክተናል ብለዋል። ዝርዝሩን የፓሪስዋ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ አዘጋጅታዋለች።
ሃይማኖት ጥሩነህ 
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ