1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለ ደቡብ አፍሪቃው «የሰላም ንግግር» ምን ይታወቃል?

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 15 2015

በሰሜን ኢትዮጵያ ለዓመታት ሲፋለሙ የቆዩት የኢትዮጵያ መንግሥት እና የትግራይ ክልል ባለሥልጣናት ተወካዮች ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ያደርጉታል ስለተባለው «የሰለም ንግግር» ብዙም የወጡ መረጃዎች የሉም። ሆኖም ዶይቸ ቬለ መረጃዎችን ለማግኘት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።

https://p.dw.com/p/4Ifdr
Äthiopien Humera Tigray Konflikt
ምስል Baz Ratner/REUTERS

ንግግሩ የፊታችን እሁድ ይጠናቀቃል ተብሏል

በሰሜን ኢትዮጵያ ለዓመታት ሲፋለሙ የቆዩት የኢትዮጵያ መንግሥት እና የትግራይ ክልል ባለሥልጣናት ተወካዮች «የሰላም ንግግር» ደቡብ አፍሪቃ፤ ፕሪቶሪያ ከተማ ውስጥ ዛሬ መጀመሩን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት (AFP) የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎዛ ቃል አቀባይ ቪንሰንት ማግዌንያን ጠቅሶ ዘግቧል። ሁለቱ ተፋላሚ ኃይላት ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ያደርጉታል ስለተባለው «የሰለም ንግግር» ብዙም የወጡ መረጃዎች የሉም። ሆኖም ዶይቸ ቬለ መረጃዎችን ለማግኘት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ያንን በተመለከተ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ከባልደረባዬ ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ጋር ተወያይተናል። 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

አዜብ ታደሰ