1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለ ካቢኔው የተሿሚዎችና ባለሞያዎች አስተያየት

ረቡዕ፣ መስከረም 26 2014

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በስድስተኛ የስሥራ ዘመን፤ አንደኛ ዓመት፤ አንደኛ ልዩ ስብሰባው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቀረበለትን ዕጩ ሚኒስትሮችን ሹመት አጽድቋል። በሁለት ተቃውሞ እና በ12 ድምጸ ተአቅቦ የፀደቀው የካቢኔ አባላቱ ሹመት ሦስት የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችንም በማካተት ነው የተጠናቀቀው።

https://p.dw.com/p/41Lhb
Äthiopien Premierminister Abiy Ahmed stellt im Parlament sein neues Kabinett vor
ምስል Ethiopian Prime Minister Office

ተሿሚዎችና ባለሞያዎች ምን ይላሉ?

የኢትዮጵያ የዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በስድስተኛ የስሥራ ዘመን፤ አንደኛ ዓመት፤ አንደኛ ልዩ ስብሰባው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቀረበለትን ዕጩ ሚኒስትሮችን ሹመት አጽድቋል። በሁለት ተቃውሞ እና በ12 ድምጸ ተአቅቦ የፀደቀው የካቢኔ አባላቱ ሹመት ሦስት የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችንም በማካተት ነው የተጠናቀቀው።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቀረቡ የፌደራል መንግስት 22 የካቢኔ አባላት (ሚኒስትሮች) ዝርዝር ውስጥ አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው አንዱ፤ የዉኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር (ዶ/ር ኢ/ር) ሀብታሙ ኢተፋ ናቸው፡፡ አስተያየታቸውንም ለዶይቼ ቬለ የሰጡት በተሰጠቻቸው ከባድ ኃላፊነት መደሰታቸውን እና መዘጋጀታቸውን በመግለጽ ነው። 

ዶ/ር ኢንጂነር ሃብታሙ በዛሬው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሎ ተመለከትኩ ያሉት የአባላቱ ሃሳብን የመግለጽ እና የተለያዩ ድምጾች የመሰማት አውድ በአዎንታዊ መልኩ የተረዱት መሆኑን አስረድተዋል።

በዛሬው የፌዴራል ካቢኔ አወቃቀር እውቅ የተቀናቃኝ ፖለቲካ ፓርቲ አመራር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትር ሆነው ተሱመዋልው። የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው የተሸሙት የአምሃራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን ሊቀመንበር አቶ በለጠ ሞላ ሌላው የተቀናቃኝ ፓርቲ አዲሱ የካቢነ አባል ናቸው። ከዚሁ ጎራ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው የተሸሙት አቶ ቀጄላ መርዳሳ አስተያየታቸውን ከሰጡን ናቸው።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶር ዮናስ አዳዬ የዛሬውን የፓርላማ ውሎ አስተያየታቸውን አዎንታዊ ገጽታው በመግለጽ ነው የጀመሩት። 
ዶ/ር ዮናስ በ14 ወንዶችና 8 ሴቶች የተዋቀረው፣ በ18 የገዢውና 3 የተቀናቃኝ የፖለቲካ አመራሮች የተዋቀረውን የሚኒስትሮች ካቢኔ በጎ ጅምር ብሆንም ሊሰፋ እና ሊያድግ የሚገባ ብለውታል።
ሥዩም ጌቱ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ