1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ

ሐሙስ፣ መጋቢት 20 2010

ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸውን በማስመልከት የተለያዩ ሃገራት መሪዎች የመልካም ምኞች መግለጫ እየላኩ ነው።

https://p.dw.com/p/2vDOV
Äthiopien Außenministerium Meles Alem
ምስል DW/Y. Egziabher

ከውጭ ሃገራት የመልካም ምኞች መግለጫ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ይህን በመጥቀስ በአካባቢውም ሆነ በርቀት የሚገኙ እና ሀገሪቱ የነበረችበት አስቸጋሪ ሁኔታ ይከታተሉ የነበሩ ሃገራት መንግሥታት መሪዎች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ገዢዉ ፓርቲ የሊቀመንበር ምርጫዉን በሰላም በማጠናቀቁ የደስታ መልዕክት እየላኩ መሆኑን ዘርዝረዋል። ሳምንታዊ በሆነዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ለሕዳሳዉ ግድብ በሚደረገው የቦንድ ሽያጭ መካከለኛዉ ምሥራቅ ከሚገኙ ዜጎች ከፍተኛው ገቢ መገኘቱም ተነግሯል። መግለጫውን የተከታተለው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን ልኮልናል።  

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ