1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሱዳን ወታደራዊ መንግሥትና የተቃዋሚዎች ስምምነት 

ሰኞ፣ ሐምሌ 1 2011

ሥልጣን የያዘው የሱዳን ወታደራዊ  ምክር ቤት እና የተቃዉሞ እንቅስቃሴ መሪዎች ሀገሪቱን በጋራ ለማስተዳደር ኻርቱም መስማማታቸው ለሱዳን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ከፍቷል። ከስምምነቱ መድረስ የቻሉት በአፍሪቃ ሕብረት እና በኢትዮጵያ አሸማጋይነት መሆኑ ቢነገርም፤ ምንጮች የዩናይትድ ስቴትስ እና የአረብ ሃገራት ተፅዕኖ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3LlPl
Sudan Khartoum | Sudans Stellvertretender Leiter des Militärrats - Mohamed Hamdan Dagalo
ምስል Getty Images/AFP/E. Hamid

ከስምምነቱ መድረስ የቻሉት በአፍሪቃ ሕብረት እና በኢትዮጵያ አሸማጋይነት ነዉ

ሥልጣን ይዞ የሚገኘዉ የሱዳን ወታደራዊ  ምክር ቤት እና የተቃዉሞ እንቅስቃሴ መሪዎች ሀገሪቱን በጋራ ለማስተዳደር መዲና ኻርቱም ከሥምምነት መድረሳቸው ለሱዳን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ከፍቷል። ዛሬ የመግባብያ ሰነዳቸዉን እንደሚጠበቀዉ ሁለቱ ወገኖች በስምምነታቸዉ መሠረት ሀገሪቱ በምትመርጠዉ ምክር ቤት ሲቪልና የጦር መኮንኖቹ በጋራና በፈረቃ እየተቀባበሉ ይመራሉ። ይህን ሦስት ዓመት የሚቆየዉን አካል አንዳንዶች የሽግግር መንግሥት ሲሉት ሌሎች በበኩላቸዉ የጣምራ መንግሥት ብለዉታል። ከስምምነቱ መድረስ የቻሉት በአፍሪቃ ሕብረት እና በኢትዮጵያ አሸማጋይነት መሆኑ ቢነገርም፤ ውስጥ አዋቂ ምንጮች የዩናይትድ ስቴትስ እና የአረብ ሃገራት ተፅዕኖ ማድረጋቸውን ለዜና አውታሮች ገልጸዋል።

 

ይልማ ኃይለሚካኤል


አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ