1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰሞነኛው የብልፅግና ፓርቲ አባላት የማኅበራዊ መገናኛ ውዝግብ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 1 2013

ሰሞኑን በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ደረጃ በማኅበራዊ መገኛ ዘዴዎች የተንሸራሸሩ፤ የማይጣጣሙ የሚመስሉ ሃሳቦች የበርካቶችን ትኩረት ይዘው ቆይቷል። ነገሩ ከአንድ ውህድ ፓርቲ አመራሮች መሆኑ ደግሞ ያወዛገባቸውም አልጠፉም።

https://p.dw.com/p/3mXRM
Logo Prosperity Party Ethiopia

«የምሁር አስተያየትና ምክር»

ሰሞኑን በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ደረጃ በማኅበራዊ መገኛ ዘዴዎች የተንሸራሸሩ፤ የማይጣጣሙ የሚመስሉ ሃሳቦች የበርካቶችን ትኩረት ይዘው ቆይቷል። ነገሩ ከአንድ ውህድ ፓርቲ አመራሮች መሆኑ ደግሞ ያወዛገባቸውም አልጠፉም። በጉዳዩ ላይ ለዶይቼ ቬለ አስተያየታቸውን ያጋሩት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝምና ሰብዓዊ መብቶች ማዕከል መምህር ዶ/ር ሲሳይ መንግሥቴ አንደሚሉት የሃሳብ ልዩነቶቹ በብልጽግና ፓርቲ ውህደት ላይ የሃሳብ ውህደቱ ገና በሂደት ላይ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል። ሀገሪቱ ባሁን ወቅት የተዋቀረችበት የብሔር እና የቋንቋ ፌዴራሊዝም ከሕብረ ብሔራዊ ፌዴራሊዝም ይለያል በሚል የሚከራከሩት የፌዴራሊዝም መምህሩ፤ አመራሮቹ ሀገር እንደሚያስተዳድር ፓርቲ ሰፋ ላሉት ውይይቶች አውድ ሊያመቻቹ ይገባልም ነው ያሉት። 

ስዩም ጌቱ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ