1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰላማዊ ሰልፍ በኦሮሚያ

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 17 2013

በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ለወራት የቀጠለውና አሁንም እልባት ባላገኘው ጦርነት የመከላከያ ሰራዊትን በመደገፍ የውጭ ጣልቃ ገብነትና የቀድሞ የትግራይ ክልል ገዥ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወኃትን) የሚነቅፍ የተባለው ሰልፉ በነገው እለትም  በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ይቀጥላል ተብሏል፡

https://p.dw.com/p/3xzGW
Äthiopien - Protest in Adama
ምስል Adama city communication affairs office

ሰላማዊ ሰልፍ በኦሮሚያ

በኦሮሚያ ክልል ለተከታታይ ቀናት ይካሄዳል የተባለው ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ በአዳማ ከተማ መካሄድ ጀመረ፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ለወራት የቀጠለውና አሁንም እልባት ባላገኘው ጦርነት የመከላከያ ሰራዊትን በመደገፍ የውጭ ጣልቃ ገብነትና የቀድሞ የትግራይ ክልል ገዥ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወኃትን) የሚነቅፍ የተባለው ሰልፉ በነገው እለትም  በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ይቀጥላል ተብሏል፡

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ በተለይም ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት በቀጣይ ቀናት ይካሄዳሉ ባሉት ሰላማዊ ሰልፎች እና ህዝባዊ ውይይቶች የሃብት ማሰባሰብ ስራም ይከናወናል ብለዋል፡፡

ስዩም ጌቱ

እሸቴ በቀለ