1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ራይድ የታክሲ አገልግሎት ስሞታ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 5 2011

በአዲስ አበባ ከተማ ለሕዝብ የማመላለሻ አገልግሎትን የሚሰጠዉ «ራይድ» በሚል መጠርያ የሚታወቀዉ ታክሲ ከ 1000 ሺህ በላይ የሚሆኑ ባለንብረቶች ከፈቃድ ሰጭ የመንግሥት አካላት ጋር ሥራዉን ለማቆም በመገደዳቸዉ ስሞታ እያቀረቡ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3A8WZ
Russische Taxi-App von Yandex
ምስል picture alliance/dpa

የራይድ አገልግሎት ስሞታ


በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ደንበኞች እና የታክሲ አገልግሎት አቅራቢዎችን የሚያገናኘው ራይድ ታክሲ እና የኢትዮጵያ መንግሥት እየተወዛገቡ ነው። የራይድ ታክሲ አባል ሆነው የታክሲ አገልግሎት የሚያቀርቡ ኢትዮጵያውያን በረባ ባልረባው በትራፊክ ፖሊሶች ቅጣት ይጣልብናል ሲሉ ለ«DW» ተናግረዋል። ኩባንያው ለወትሮው በአዲስ አበባ ከተለመዱት የታክሲ አገልግሎት አቅራቢዎች የተለዩ እና የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ ተሽከርካሪዎችን በአባልነት በማቀፍ በአጭር የጽሁፍ መልዕክት ከተጓዦች ያገናኛል። የኢትዮጵያ መንግሥት ተቋማት ግን ኩባንያው እንዲህ አይነት ግልጋሎት እንዲያቀርብ ፈቃድ አልተሰጠውም እያሉ ነው። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባዉን ልኮልናል። 


ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ 

አዜብ ታደሰ  
እሸቴ በቀለ