1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ራይላ ኦዲንጋ የኬንያ ተቃዋሚዎች እጩ ሆነው ቀረቡ 

ዓርብ፣ ሚያዝያ 20 2009

የኬንያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመጪው ነሐሴ ለሚደረገው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ራይላ ኦዲንጋን እጩ አድረገው መርጠዋል።

https://p.dw.com/p/2c64U
Raila Odinga ARCHIV Trauer
ምስል Till Muellenmeister/AFP/Getty Images

MMT / Q&A Kenya Primary election******* - MP3-Stereo

 የ72 አመቱ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒሥትር ራይላ ኦዲንጋ  ብሔራዊ ላዕላይ ትብብር (National Super Alliance) የተባለው ጥምረት ይፋ እጩ ናቸው። ራይላ ኦዲንጋ ለኬንያ የፕሬዝዳንትነት መንበረ ሥልጣን ሲገዳደሩ ሁለተኛቸው መሆኑ ነው።ኦዲንጋ በእጩነት መቅረባቸውን ካረጋገጡ በኋላ «ኬንያውያንን ከግብፅ ወደ እስራኤል አሻግራችኋለሁ» ሲሉ ቃል ገብተዋል። ተቃዋሚዎቹ ኦዲንጋን በእጩነት ሲመርጡ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት የግል ፍላጎቶቻቸውን መስዋዕት ማድረጋቸውን ተናግረዋል። ኬንያ ከዚህ ቀደም ባካሔደችው ምርጫ ደም አፋሳሽ ግጭት አስተናግዳለች።

 ፍቅረማርያም መኮንን  

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሐመድ