1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመናውያንን ጭቆና የተቃወሙት የካሜሮን ንጉስ

Henri Fotso
ሐሙስ፣ ኅዳር 10 2013

ሩዶልፍ ዳውላ ማንጋ ቤል ከፍተኛ ትምህርታቸውን የተከታተሉት በጀርመንዋ ቦን ከተማ ነበር። የህግ ተማሪ ነበሩ። ኃላ ላይ ወደ ሀገራቸው የአሁኗ ካሜሮን ሲመለሱ ግን ቀኝ ገዢዋ ጀርመን ህዝባቸውን እየጨቆነች እንደሆነ ተሰማቸው። ይህን ተቃውመው ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጠውን የህይወት መስዋዕትነት ከፍለዋል።

https://p.dw.com/p/3lMp1
Zeichnung African-Roots-Beitrag

ሩዶልፍ ዳውላ ማንጋ ቤል ማን ነበሩ?
ሩዶልፍ ዳውላ ማንጋ ቤል እ ጎ አ 1873 ዓ ም ዳውላ ውስጥ ተወለዱ። እሳቸውም የንጉስ ንዱምቤ ሎቤ ቤል የልጅ ልጅ ነበሩ። ባጭሩ ንጉስ ቤል የሚባሉት አያታቸው ከጀርመን ዘውዳዊ አገዛዝ ጋር «የከለላ ውል» የተባለውን ስምምነት  በጎርጎሮሳዊው 1884 ዓም ተፈራርመው ነበር።
ሩዶልፍ ዳውላ ማንጋ ቤል ትምህርታቸውን ጀርመን ሀገር ላይ ተከታትለዋል። ኃላ ግን ዛሬ ካሜሮን ተብላ የምትጠራው ሀገር አባታቸውን ኦጉስቴ ማንጋ ንዱምቤ ቤልን ለማገዝ ተመልሰዋል። ከመስከረም 2 ቀን 1908 አንስቶም አባታቸውን ተክተው የዳውላ ሥርወ መንግሥትን ያስተዳድሩ ነበር።

ሩዶልፍ ዳውላ ማንጋ ቤልን ከቀኝ ገዢዋ ጀርመን ጋር ያላስማማቸው ነገር ምንድን ነው?

የጀርመናውያንን ጭቆና የተቃወሙት የካሜሮን ንጉስ

ዳውላ ማንጋ ቤል የጀርመን ሕግ የተወሰነ ግንዛቤ ስለነበራቸው፣ አንዳንድ ምንጮች እንደሚሉት ደግሞ በቦን ዩኒቨርሲቲ ሕግ በማጥናታቸው የተነሳ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ከቅኝ ገዢው አስተዳደር ጋር የመሥራት ዕድል ነበራቸው። ይሁንና ብዙም ሳይቆይ ቅኝ ገዥዎቹ የራሳቸውን ደንብ የማያከብሩ ሆነው አግኝተዋቸዋል። እሳቸውም ለሁለት አመት ያህል ካገለገሉ በኋላ ታማኞቻቸው ጀርመናውያኑ የከፋፈሏት ሀገራቸውን እንዲያስመልሱላቸው ሾመዋቸዋል። እንደ ንጉስ ዳውላ ማንጋ ቤል ከሆነ ጀርመን ከአያታቸው ጋር የተረራረመችውን ስምምነት የጣሰ ድርጊት ሀገራቸው ላይ ተፈፅሟል። 

ይህም ዳውላ ውስጥ በወቅቱ አንድ ለአውሮፓውያን ሌላ ደግሞ ለጥቁር ሰዎች ተብሎ የተከፋፈለ ሰፈር ነበር። ጀርመናውያኑ የፕላቱ ጆስ (በአሁኑ ጊዜ የቦናንጆ አስተዳደር)ተወላጆችን የወባ በሽታን ያሰራጫሉ በማለት ይወነጁሏቸው ብቻ ሳይሆን ዜጎቿቸውም ጋር እንዳይደርሱ ያባርሯቸው ነበር።  

ሩዶልፍ ዳውላ ማንጋ ቤል ውጊያውን እንዴት ይመሩ ነበር?

ሩዶልፍ ዳውላ ማንጋ ቤል ራቅ ካለ ቦታ ሆነው አመፁን ያካሂዱ ነበር። ያላቸውንም  የግንኙነት መረብ አስፍተው ተመሳሳይ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ጋር በመሆን ካሜሮን ውስጥ አጋሮች ለመፍጠር ችለው ነበር።  ትግላቸው በራሽታግ (ጀርመን ፓርላማ) ያሉ የአንድን ህዝብ ዕድል በራስ የመወሰን መብት የሚቀበሉ ሶሻል ዲሞክራቶች ዘንድ ሳይቀር ተሰሚነት አግኝቷል። ዳውላ ማንጋ ቤል የህግ ተማሪ ስለነበሩም ትግላቸውን የጀመሩት እሳው የተማሩትን ህግጋቶች ተጠቅመው ነበር። ይህ ሁሉ እንደማይሰራ የተረዱ ጊዜ ግን  ዝነኛዎቹ የዳውላ ተቃውሞ ሰልፎች ለመዞር ወሰኑ። 

Zeichnung African-Roots-Beitrag

ሩዶልፍ ዳውላ ማንጋ ቤል እንዴት ሞቱ?

በ 1914 የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ሲጀመር ጀርመኖች ሁሉንም አመፆች በአጭሩ ለመቅጨት ሞክረዋል። በመሆኑም የጀርመን አስተዳደር ሩዶልፍ ዳውላ ማንጋ ቤልን ነሐሴ 7 ቀን 1914 በቁጥጥር ስር አውሎ በከባድ የአገር ክህደት ወንጀል የሞት ፍርድ ፈርዶባቸዋል። የዛኑ ዕለትም ኮሎኔል ሲመርማን ባልተጠበቀ ሁኔታ የቤል ሰንሰለት ወልቆ  ባለቤታቸውን ንግስቲቱንና እና ልጆቻቸውን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲሰናበቱ ፈቅደውላቸዋል። ዳውላ ማንጋ ቤል ለማምለጥ መሞከር ይችሉ ነበር ነገር ግን በማግስቱ ነሐሴ 8 ቀን ፍርድ ቦታቸው ቀርበው በአደባባይ ተሰቅለው ተገድለዋል።  የመጨረሻ ቃላቸው “የንጹሃንን ደም ነው የምትሰቅሉት ፣ ውጤቱ በጣም የከፋ ይሆናል” የሚል ነበር።
ሩዶልፍ ዳውላ ማንጋ ቤል በካሜሮናውያን ዘንድ እንዴት ይታወሳሉ?

ዳውላ ማንጋ ቤል በቅኝ ገዥዎች ላይ የዘመቱ ሰማዕት እና ጀግና ሆነው ይታወሳል። ከዚህም ባሻገር አንዳንድ የታሪክ ምሁራን እንደሚሉት የማንጋ ቤል አመፅ የካሜሮን ነፃነትን የወለደው ሳይሆን አይቀርም። 

ሩዶልፍ ዳውላ ማንጋ ቤል: የጀርመናውያንን ጭቆና የተቃወሙት የካሜሮን ንጉስ

ይህ ዘገባ አፍሪካዊ ሥረ-መሠረት በሚል ከጌርዳ ሔንክል ተቋም ጋር በመተባበር የሚቀርብ ዝግጅት ነው። የዘገባው ሳይንሳዊ ምክር የተገኘው ከፕሮፌሰር ጉዳዬ ኮናቴ፣ ሊሊ ማፌላ Ph.D እና ፕሩፌሰር ክሪስቶፈር ኦግቦግቦ ነው።